የዘንድሮው የተመድ ኮፕ 28 አየር ንብረት ለውጥ በዱባይ እየተካሄደ ይገኛል
ተመድ የፓሪስ ስምምነትን አፈጻጸም መገምገሙን አስታወቀ፡፡
በአረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ 10ኛ ቀኑን ይዟል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየዓመቱ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የዓለም ሀገራት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎችን እና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት ጋር በመምከር ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ ጉባኤ ላይ ምድራችን በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚደርስ ጉዳትን መቀነስ የሚያስችሉ ምክክሮች እና ውይይቶች በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ አማካሪ ቡድን ከስምንት ዓመት በፊት የዓለም ሀገራት የተስማሙበት የፓሪስ ስምምነትን መገምገሙ ተገልጿል፡፡
ይህ የባለሙያዎች ቡድንም ከኮፕ28 ጉባኤ ጎን ለጎን በፈረንጆቹ 2015 የተደረሰውን የፓሪስ ስምምነት አፈጻጸም ሪፖርት ይፋ አደርጋለሁ ብሏል፡፡
በዚህ ሪፖርት መሰረትም በቀጣይ የዓለም አየር ንበረት ለውጥ ጉዳቶችን መቀነስ የሚያስችሉ ተጨማሪ ምክረ ሀሳቦች ይቀርቡበታልም ተብሏል፡፡
የፓሪስ ስምምነት የምድር ሙቀት ከ1 ነጥብ 5 ድግሪ ሴልሺየስ እንዳይበልጥ የሚያደርጉ የተለያዩ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከያ መንገዶችን መከተል የሚያስችሉ ዘዴዎችን መተግበር ላይ ያለመ ነው፡፡