ሶማሊያን በእስላማዊ የሼሪአ ህግ ለማስተዳደር የሚፈልገው አልሸባብ ከፈረንጆቹ 2006 ጀምሮ ደምአፋሳሽ ግጭት ውስጥ ከቷታል
የተመድ የጸጥታው ም/ቤት በሶማሊያ ላይ የጣለውን ለ30 አመታት የዘለቀውን ማዕቀብ ለማንሳት ድምጽ ሊሰጥ ነው።
የተመድ የጸጥታው ምክርቤት ለሶማሊያ መንግስት እና የጸጥታ ኃይሎቹ የጦር መሳሪያ እንዳይሰጥ የሚከለክለውን ማዕቀብ ለማንሳት ድምጽ እንደሚረጥ ሮይተርስ ዘግቧል።
የጸጥታው ም/ቤት በፈረንጆቹ 1992 በሶሚሊያ ላይ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ የጣለው፣ የሀገሪቱን መሪ መሀመድ ሲያድ ባሬን ያስወገዱት ተቀናቃኝ ታጣቂዎች መሳሪያ እንዳይደርሳቸው ለማድረግ ነበር።
15 አባላት ያሉት የጸጥታው ምክርቤት በእንግሊዝ የቀረቡለትን ሁለት የውሳኔ ሀሳቦች ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። በሶማሊያ ላይ ተጥሎ የነበረው ሁሉም አይነት የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንዲነሳ እና በአል ሸባብ ላይ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንዲጣል የሚሉ የውሳኔ ሀሳቦች ናቸው በእኔግሊዝ የቀረቡት።
በሶማሊያ መንግስት ላይ ምንም አይነት የጦር መሳሪያ ማዕቀብ መኖር እንደሌለበት በአንደኛው ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተጠቅሷል።
በሀገሪቱ ደህንነቱ የተጠበቀ የመሳሪያ ማከማቻ ቦታ ቁጥር ላይ ስጋቱን የገለጸው የውሳኔ ሀሳቡ ግንባታ እንዲደረግ እና ሌሎች ሀገራት እርዳታ እንዲያደርጉ ጠይቋል።
ሶማሊያን በእስላማዊ የሼሪአ ህግ ለማስተዳደር የሚፈልገው አልሸባብ ከፈረንጆቹ 2006 ጀምሮ ደምአፋሳሽ ግጭት ውስጥ ከቷታል።
የሶማሊያ መንግስት ማዕቀቡ እንዲነሳለት ለረጅም ጊዜ ሲጠይቅ ቆይቷል።
የጸጥታው ም/ቤትም ከ2013 ጀምሮ ማዕቀቡን በከፊል ማንሳት ጀምሯል።
የሶማሊያ ፕሬዝደንት ሀሰን ሼህ መሀመድ ባለፈው ሳምንት እንደተናገሩት ሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ከሚወጣበት በፊት አልሸባብን ለማጥፋት አንድ አመት ብቻ ነው የቀራት ሲሉ ተናግረዋል።