“ሱዳናውያን የገጠማቸውን ቀውስ ለመፍታት ውስን ጊዜ ነው ያላቸው” - ተመድ
ለተቃውሞ አደባባይ በወጡ ሱዳናውያን ላይ ያልተገቡ እርምጃዎች ን የወሰዱ መጠየቅ እንዳለባቸውም ተመድ አሳስቧል
ውሱን ለመፍታት የሃገሪቱ ባለስልጣናት ከፍ ያለ ድርሻ አላቸው ተብሏል
ሱዳናውያን በሀገሪቱ ያለውን ቀውስ ለመፍታት ያላቸው ጊዜ ውስን መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጸ፡፡
በካርቱም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተልዕኮ ኃላፊ ቮከር ፐርዝ ፤ “የሱዳን አጠቃላይ ሁኔታ አስጊ በመሆኑ ለችግሩ አስቸኳይ መፍትሄ ይፈልጋል” ብለዋል፡፡
ተወካዩ ትናንት ማክሰኞ ለድርጅቱ የጸጥታው ምክር ቤት በሱዳን ብዙ የሚያሰጋ ነገር አለ ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ሱዳን፤ አቶ ደመቀ ከሰሞኑ ለምክር ቤት የሰጡትን ማብራሪያ አወገዘች
“የሀገሪቱን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ማረጋጋትን ጨምሮ፣ ሱዳናውያን ፖለቲካዊ መፍትሄ ላይ ለመድረስና መፍትሄ ለማምጣት ያላቸው ጊዜ ውስን ነው”ም ነው ተወካዩ ያሉት፡፡
ቮከር ተመድ በሱዳን የተቀናጀ ሽግግር ያለውን የርዳታ ተልእኮ ይመራሉ፡፡ ተልዕኮው ከአፍሪካ ህብረትና ኢጋድ ጋር ተቀናጅቶ የሚሰራ ነው፡፡
ቮከር በሱዳን ያለውን የሽግግር ሂደት እውን ለማድረግ የሱዳናውያን በተለይም የባለስልጣናቱ ድርሻ ከፍ ያለ መሆን እንዳለበት ለምክር ቤቱ ገልጸዋል፡፡
ከአሁን ቀደም በተካሄዱ ተከታታይ ተቃውሞዎች የተወሰዱ እርምጃዎች ነገሮችን ማባባሳቸውን በመጠቆምም ታስረው የነበሩ 86 ሱዳናውያን መለቀቃቸው ፖለቲካዊ ውጥረቱን ሊያረግብ ይችላል ብለዋል፡፡
ሆኖም አሁንም በሰልፈኞች ላይ ያልተገባ እርምጃ የወሰዱና ሰብዓዊ ጥሰት የፈጸሙ አካላትን ተጠያቂ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የፖለቲካ ስምምነት ከተደረሰ በኋላ የጁባ የሰላም ስምምነትን ጨምሮ ሌሎች የግጭቱን መንስኤዎች የሚፈቱ ቁልፍ ፕሮቶኮሎችን ተግባራዊ ለማድረግ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ ያስፈልጋልም ብለዋል ቮከር።
በሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን የሚመራው የሃገሪቱ ወታደራዊ የሽግግር መንግስት ቮከርን በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ እየገቡ ነው በሚል ሊያባርራቸው እንደሚችል ደጋግሞ ማስጠንቀቁ ይታወሳል፡፡