እስራኤል በጋዛ የዘር ማጥፋት ተግባርና ጾታዊ ጥቃት ፈጽማለች ሲሉ የተመድ ባለሙያዎች ከሰሱ
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኔያሁ "እድሎአዊና ጸረ-ጽዮናዊ" ነው በማለት የሪፖርቱን ግኝት ውድቅ አድርገውታል

ሪፖርቱ እንደገለጸው የእስራኤል ኃይሎች ፍልስጤማውያንን ልብሳቸውን በመግፈፍ በአደባባይ እርቃናቸውን እንዲታዩ አድርገዋል፤ ወሲባዊ ጥቃትም ፈጽመውባቸዋል
እስራኤል በጋዛ የዘር ማጥፋት ተግባርና ጾታዊ ጥቃት ፈጽማለች ሲሉ የተመድ ባለሙያዎች ከሰሱ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ባለሙያዎች እስራኤል በጋዛው ጦርነት ወቅት የሴቶችን የጤና ተቋማት በስልት በማውደም በፍልስጤማውያን ላይ የዘር ማጥፋት ተግባር ማካሄዷንና ጾታዊ ጥቃትን እንደጦርነት ስትራተጂ መጠቀሟን በትናንትናው እለት ባወጡት ሪፖርት ገልጸዋል።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኔያሁ "እድሎአዊና ጸረ-ጽዮናዊ" ነው በማለት የሪፖርቱን ግኝት ውድቅ አድርገውታል።
" ተመድ ሽብርተኛው ሀማስ በፈጸማችው በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችና የጦር ወንጀሎች ላይ ከማተኮር ይልቅ እስራኤል በሀሰተኛ ክስ በድጋሚ ማጥቃትን መርጧል" ብለዋል ኔታንያሁ ባወጡት መግለጫ።
"የእስራኤል ባለስልጣናት የወሊድ መጠንን ለመቀነስ ያለሙ ክልከላዎችን በመጣል ጭምር የፍልስጤማውያንን የወሊድ አቅም በማዳከም በሮም ስታቱና በጀኖሳይድ ኮንቬንሽን የዘር ማጥፋት ተግባር ውስጥ አንዱ የሆነውን ተግባር ፈጽመዋል" ሲል ምስራቅ እየሩሳሌምንና እስራኤልን ጨምሮ በእስራኤል በተወረሩ ቦታዎች ላይ ምርመራ ያደረገው የተመድ ነጻ አለምአቀፍ ኮሚሽን በሪፖርቱ ገልጿል።
በህክምና አገልግሎቶች ላይ ገደብ በመጣሉ ምክንያት የእናቶች ሞት መጨመሩንና ይህም የሰው ዘርን ከማጥፋት ጋር የሚከስተካከል እንደሆነ ኮሚሽኑ ጠቅሷል
ሪፖርቱ እንደገለጸው ሀማስ ጥቅምት 7፣2023 በእስራኤል ላይ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ የእስራኤል ኃይሎች በሀማስ ላይ በከፈቱት ዘመቻ ፍልስጤማውያንን ልብሳቸውን በመግፈፍ በአደባባይ እርቃናቸውን እንዲታዩ አድርገዋል፤ ወሲባዊ ጥቃትም ፈጽመውባቸዋል።
እስራኤል ግን የቀሰቡባትን ክሶች አስተባብላለች።