ከህወሓት የውስጥ ሽኩቻ ጋር ተያይዞ ስሟ የተነሳው ኤርትራ ምን ምላሽ ሰጠች?
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር “ኤርትራ የፕሪቶርያውን የሰላም ስምምነት የማፍረስ ፍላጎት የላትም” ብለዋል

አቶ ጌታቸው “ከትግራይ ክልል ትርምስ እናተርፋለን የሚሉ አካላት ውሰጥ የኤርትራ መንግስት አንዱ ነው” ብለዋል
የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል “ኤርትራ የፕሪቶርያውን የሰላም ስምምነት የማፍረስ ፍላጎት የላትም” ብለዋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ትናንት በሰጡት መግለጫ “ከትግራይ ክልል ትርምስ እናተርፋለን የሚሉ አካላት ውሰጥ የኤርትራ መንግስት አንዱ ነው” ማለታቸው ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎም የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ኤክስ (የቀድሞ ትዊተር) ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ ኤርትራ በህወሓት የፖለቲካ ቡድኖች ውስጥ ያለውን የውስጥ ሽኩቻ የማባባስ ፍላጎት የላትም ብለዋል።
ምክንያቱም በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው የውስጥ ሽኩቻ ማባባስ በትግራይ ህዝብ ላይ አላስፈላጊ እና ሊወገድ የማይችል ስቃይ የሚያስከት መሆኑን አክለዋል።
ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ጋር በተያያዘም የማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ ገብረመስቀል፤ “ኤርትራ የፕሪቶርያውን የሰላም ስምምነት የማፍረስ ፍላጎት የላትም” ብለዋል።
የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ “ከዚህ ቀደም በተለያዩ አጋጣሚዎች በማያሻማ መልኩ እንደተገለጸው፣ ኤርትራ የፕሪቶሪያን የሰላም ስምምነት ለማፍረስ ምንም ፍላጎት የላትም” ሲሉ ገልጸዋል።
የማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ ገብረመስቀል አክለውም፤ ከኤርት ጦር ጋር በተያያዘ ጦሩ አሁንም የትግይ ክልል አካባቢዎች ውስጥ አለ በሚል በተወሰኑ አካላት የሚሰነዘረው ሀሳብ “የሀሰት ውንጅላ እና ግጭት መቀስቀስ የፈለጉ አካላት የሚፈጥሩት ምክንያት ነው” ብለዋል።
የኤርትራ ጦር አባላት ሙሉ በሙሉ በሀገራቸው ሉዓላዊ ግዛት ውስጥ ተሰማርተው እንደሚገኙም ነው ሚኒስትሩ ያስታወቁት።
ከቀይ ባህር ጋር በተያያዘም የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች በየጊዜው የሚያወጡት ግጭት ቀስቃሽ መግለጫዎች አላስፈላጊ እና ውጥረት የሚያባብሱ ሆነው ቀጥለዋል ብለዋል ሚኒትሩ የማነ ገብረመስቀል።
እንዲህ አይነት እንቅስቀሴዎች ያለምንም ማወላወል በጠንካራ ቃላት መወገዝ እንዳለበትም ሚኒስተሩ አሳስበዋል።
“ከትግራይ ክልል የፖቲካ አለመረጋት ጋር ተያይዞ የኤርትራ ስም ከሰሞኑ በተደጋጋሚ ሲነሳ ተስተውሏል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ትናነን በአዲስ አበባ በሰጡት መግለጫም “ከትግራይ ክልል ትርምስ እናተርፋለን የሚሉ አካላት ውሰጥ የኤርትራ መንግስት አንዱ ነው” ማታው ይታወሳል።
አቶ ጌታው በመግለጫቸው፤ “ህገ ወጥ እንቅስቃሴ ከሚያደርጉ ከወታደራዊ እና ፖለቲካዊ አመራሮች መካከል ከኤርትራ ጋር ግንኙነት ያላቸው አካላት እንዳሉ እናውቃለን” ብለዋል።
የኤርትራ ፍላጎት የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራ መንግስትን ይወራል ብለው በሚሰጉበት ሰአት ትግራይን እንደ መሸሸጊያ መጠቀም አሊያም ጠንከር ያለ አጋጣሚ ተፈጥሯል ብለው ካመኑ ከትግራይ ጋር በመሆን ወደ አዲስ አበባ ማማተር ሊሆን እንደሚችልም ገልጸዋል።
በዚህ ጉዳይ ውስጥ አንዳንድ የፖለቲካ ኃይል ወይም የፀጥታ ኃላፊ ከነሱ ጋር በማበር ለመሥራት ማሰቡ አስደንጋጭ ነው በማለትም በመግለጫቸው ላይ ጠቅሰዋል።