የተመድ የምግብ ኤጀንሲ በሰሜን ዳርፉር ግዛት የሚያሰራጨውን እርዳታ አቆመ
ተመድ ስራዎን ያቆመው “በቅርቡ በመጋዘኖቹ ላይ የደረሰውን ጥቃት” ተከትሎ መሆኑን አስታውቋል
ተመድ እርዳታ ማቆሙን ተከትሎ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ የአካባቢውን ነዋሪዎች ለአደጋ እንዳይጋለጡ ተሰግቷል
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሱዳን ሰሜን ዳርፉር ግዛት በቅርቡ በመጋዘኖቹ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ስራውን ማቆሙ የሚታወቅ ነው።
ይሁን እንጅ ውሳኔው ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ የአካባቢውን ነዋሪዎች ለአደጋ የሚያጋልጥ መሆኑን ነው የሲጂቲኤን ዘገባ የሚያመለክተው፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ)የምግብ ኤጀንሲ ባወጣው መግለጫ በአካባቢው የሚገኙት ሶስቱም መጋዘኖች ጥቃት ደርሶባቸዋል ተዘርፏል ብሏል። ከ5 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ምግብ መሰረቁንም ቡድኑ ገልጿል።
በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ማንነቱ ያልታወቀ የታጠቀ ቡድን በሰሜን ዳርፉር ግዛት ኤል-ፋሸር ውስጥ ከሚገኙት መጋዘኖቹ በአንዱ ላይ ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ፤ የአካባቢው ባለስልጣናት በግዛቱ ዙሪያ የሰዓት እላፊ ገደብ መጣላቸውም ነው የዓለም የምግብ ፕሮግራም ያስታወቀው።
የዓለም የምግብ ፕሮግራም አክሎ“ እስከ ሃሙስ ጠዋት ድረስ በቀጠለው ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ዘራፊዎች በርካታ የመጋዘን ግንባታዎችን አፍርሷል”ም ብሏል::
የ ደብሊው ኤፍ ፒ / WFP/ ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሊ በበኩላቸው "ስርቆቱ ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን የሚያስፈልጋቸውን የምግብ እና የስነ-ምግብ ድጋፍ ያክል የተዘረፈበት"መሆኑን ገልጿል፡፡
"ይህ በመላ ሀገሪቱ በምናደርገው እንቅስቃሴ ላይ ትልቅ ውድቀት ብቻ ሳይሆን ሰራተኞቻችንን አደጋ ላይ የሚጥል እና በጣም ተጋላጭ የሆኑትን ቤተሰቦች ፍላጎት የማሟላት አቅማችንን አደጋ ላይ የሚጥል ነው" ሲሉም አክሏል ዋና ዳይሬክተሩ፡፡