የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል ተሰግቷል
በሱዳን ዳርፉር በተቀሰቀሰ ግጭት 199 ሰዎች መሞታቸውን የአገሪቱ የሐኪሞች ማህበር ገለጸ፡፡
ማህበሩ ግጭቱ በጎሳ ልዩነት ምክንያት የመጣ ነው ያለው ኮሚቴው አረብ ነን በሚሉ እና በሌሎች ጎሳዎች መካከል መቀስቀሱን አስታውቋል፡፡
በዚያው በዳርፉር ምዕራባዊ አካባቢዎች ሌላ አዲስ ግጭት ተቀስቀሶ የሰዎች ህይወት ማለፉን የገለጸው ማህበሩ የሟቾቹን ቁጥር ለማወቅ በማጣራት ላይ ነኝ ብሏል፡፡
የአይሲሲ አቃቤ ህግ ሱዳን የዳርፉር ተጠርጣሪዎችን አሳልፋ እንድትሰጥ አሳሰበ
በዳርፉር ግዛት እንዲህ ዐይነት ጎሳን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች በተደጋጋሚ ያጋጥማሉ፡፡ ከባለፉት ሁለት ወራት ወዲህ ግን ይበልጥ ተደጋግመዋል፤ የሃገሪቱን መንግስት “ተገቢውን እርምጃ አልወሰደም” በሚል እንደሚወቅሰው እንደ ማህበሩ ገለጻ፡፡
የሱዳን መንግስት ግጭቱን ለማስቆም ከሁሉም ክፍል የተውጣጣ 3 ሺህ አባላት ያሉት ጦር ወደ ዳርፉር እንደሚልክ ቢያስታውቅም ተግባራዊ አላደረገውም፡፡
የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት ኤል ሃዲ እድሪስ (ዶ/ር) ወደ ስፍራው በማቅናት ጉብኝት አድርገው የአካባቢውን ነዋሪዎች አነጋግረው ተመልሰዋል፡፡
በምዕራብ ዳርፉር ለ137 ሰዎች ሞት ምክንያት በሆነው ግጭት ዙሪያ ምርመራ እነዲደረግ ተመድ አስጠነቀቀ
የሱዳን መንግስት እና በአካባቢው ይንቀሳቀሱ የነበሩ ተፋላሚ ሀይሎች ከአንድ ዓመት በፊት በደቡብ ሱዳን መዲና ጁባ ግጭቱን ለማስቆም በጋራ ሊሰሩ ስምምነት ተፈራርመው ነበር፡፡
በዚህ ስምምነት መሰረትም ለ17 ዓመት የቀጠለውን የዳርፉር ግጭት በማስቆም እና በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ከመንግስት ጦር ጋር ተቀናጅተው እንዲሰሩ ቢስማሙም ግጭቱን ማስቆም አልተቻልም፡፡