የህክምና ቁሳቁሶች ከደረሱም 10 ቀናት አልፈዋል
የተባበት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ቃል አቀባይ ስቴፈን ዱጃሪክ በአካባቢው ያሉትን የአለም የምግብ ፕሮግራም የእርዳታ ስርጭት ስፍራዎች የስጋት ቀጠና ሆነዋል ብለዋል።
በአካባቢው የእስራኤል ጦር መጠኑ ከፍ ያለ ወታደራዊ ዘመቻ በማከነዋን ላይ ሲሆን በዚህ የተነሳም 1ሚልዮን የሚጠጉ ሰዎች ለምግብ እጥረት ተጋላጭ መሆናቸው ነው የተሰማው፡፡
በራፋ በኩል ዋነኛ የሰብአዊ እርዳታ ማጓጓዣ የነበረው መተላለፍያ ከተዘጋ ሁለት ሳምንታት ያስቆጠረ ሲሆን በዚህ ከቀጠለም ከፍተኛ ተፈናቆዮች በሚገኙበት በዚህ ስፍራ ሰብአዊ ሁኔታዎች ሊከፉ እንደሚችሉ ሲጂኤን ዘግቧል።
የአለም ጤና ድርጅት ሀላፊ ዶክተር ቴዎድሮስ በአካባቢው በሚካሄደው ከፍተኛ ውግያ ምክንያት በአስከፊ ሁኔታ ላይ የሚገኙ 700 ታማሚዎች እና 148 የጤና ባለሙያዎችን ማስወጣት አልተቻለም ብለዋል፡፡
የራፋ ድንበር መዘጋትን ተከትሎ አሜሪካ ተመድ እና ሌሎች የሰበአዊ ድጋፍ የሚያደርጉ አካላት አማራጭ የእርዳታ ማስተላለፍያ መንገዶችን በማፈላለግ ላይ ናቸው።
8ተኛ ወሩን ባስቆጠረው የጋዛ ጦርነት ከ35 ሺ የሚሻገሩ ንጹሀን ህይወታቸው አልፏል፡፡