ተመድ በጥላቻ ንግግርና 'አደገኛ' መልዕክቶች ላይ የበለጠ እርምጃ እንዲወስድ አሳሰበ
ኩባንያዎች የጥላቻ ንግግርን በተመለከተ ለሚሰሩትና ላልሰሩ ነገር ተጠያቂ መሆን አለባቸው ብለዋል

በጋዜጠኞችና በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ላይ ያለአግባብ ጥቅም ላይ የሚውሉ የጥላቻ ንግግር ህጎች መዛመታቸው ተነግሯል
የተመድ የመብቶች ኮሚሽነር በጥላቻ ንግግርና 'አደገኛ' መልዕክቶች ላይ የበለጠ እርምጃ እንዲወስድ አሳሰቡ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመብት ኃላፊ የጥላቻ ንግግርና አደገኛ መልዕክቶችን "ሰፊ ስርጭት" መከላከልን ጨምሮ ለመቆጣጠር የተቀናጀ ዓለም አቀፍ ጥረቶች እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
እሁድ ከሚከበረው ዓለም አቀፍ የጸረ-ጥላቻ ንግግር መከላከል ቀን በፊት፣ ቮልከር ተርክ "ትልቅ ግብዓት ያለው ጥረት" ዓለምን ከመከራ ሊያጸዳው እንደሚችል ገልጸዋል።
"የጥላቻ መስፋፋት መለያየትን ለመዝራት፣ ለማፍረስ እና ከትክክለኛ ጉዳዮች ለማዘናጋት በሚፈልጉ አካላት እንደሚሰራጭ እናውቃለን" ብለዋል።
የማህበራዊ ሚዲያው በተለይም "ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ተደራሽነትን እና ፍጥነትን በመስጠት ለጥላቻ ንግግር ምቹ ሜዳ ሆኗል" ሲሉ በመግለጫቸው ገልጸዋል።
"ጥላቻ ትምክህተኝነትን፣ አድልዎንና አመጽን ያነሳሳል" ሲሉም አክለዋል።
ሱዳን በተመድ የፀጥታው ም/ቤት ስብሰባ ላይ ስለ ኢትዮጵያ ምን አለችʔ
የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር "ዓለማችንን ከጥላቻ የሚያጸዳው ጥይት፣ ማብሪያ ማጥፊያ የለውም" ሲሉም ተናግረዋል።
ነገር ግን የታለሙ እርምጃዎች ላይ ቢሰራ የጥላቻ ንግግሮችን ስርጭት መገደብ እና የሚያሰራጩትን ተጠያቂ ማድረግ እንደሚቻል ገልጸዋል።
በተጨማሪ ኩባንያዎች የጥላቻ ንግግርን በተመለከተ ለሚሰሩት እና ላልሰሩ ነገር ተጠያቂ መሆን አለባቸው ብለዋል።
"ጥላቻን የሚያቋርጡ አውታረ መረቦችን መገንባት እና ድምጾችን ማጉላት አለብን" በማለት ለአብነት የኃይማኖት መሪዎች ለጥላቻ እና ለአመጽ ማነሳሳት ምላሽ እንዲሰጡ ማድረግን ጠቁመዋል።
"በአለም አቀፍ ደረጃ በጋዜጠኞች እና በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ላይ ያለአግባብ ጥቅም ላይ የሚውሉት ከጥላቻ ንግግር ጋር የተገናኙ ህጎች መስፋፋታቸው የጥላቻ ንግግርን ከማስፋፋት ባልተናነሰ ጉዳት ያለው ነው" ብለዋል።