ተመድ አሜሪካ በገነባችው መሸጋገሪያ ድልድይ ለጋዛ እርዳታ ማቅረብ ጀመረ
ተመድ እንደገለጸው ወደ ጋዛ ቢያንስ 500 እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በየቀኑ ማስገባት ያስፈልጋል
እስራኤል የሀማስ የመጨረሻ ምሽግ ይገኝባታል የምትላትን የራፋ ከተማ እንዳታጠቃ ጫና ቢደረግባትም ሳትቀበለው ቀርታለች
ተመድ አሜሪካ በገነባችው መሸጋገሪያ ድልድይ ለጋዛ እርዳታ ማቅረብ ጀመረ።
የተባበሩት መንግስታ ድርጅት(ተመድ) ለጋዛ የሚያቀርበውን እርዳታ ካቋረጠ ከሁለት ቀናት በኋላ አሜሪካ በገነባችው መሸጋገሪያ ድልድይ በመጠቀም በድጋሚ ማቅረብ መጀመሩን አስታውቋል።
እስራል ወደ ጋዛ ተጨማሪ እርዳታ እንዲገባ እንድትፈቅድ የሚደረግባት ጫና እያየለ በመጣበት ወቅት ነው እርዳታው አሜሪካ ወደ ገነባችው ማሸጋገሪያ ቦታ የደረሰው።
ተመድ በጋዛ ያለውን ቀውስ ማቃለል የሚቻለው በየብስ እርዳታ ማስገባት ሲቻል እንደሆነ ቢያምንም፣ አሜሪካ በዘረጋችው የባህር ላይ ተንሳፋፊ ማስተላለፊያ ድልድይ የሚቀርበውን እርዳታ እያስተባበረ ይገኛል።
ተመድ እንደገለጸው ወደ ጋዛ ቢያንስ 500 እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በየቀኑ ማስገባት ያስፈልጋል።
10 እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በተመድ ኮንትራክተሮች አማካኝነት ተጓጉዘው ዴየር አልባላህ በሚገኘው የዓለም የምግብ ፕሮግራም ማከማቻ በዛሬው እለት ተራግፈዋል።
ነገርግን ባለፈው ቅዳሜ 11 የሚሆኑ ተሸከርካሪዎች መንገድ ላይ በችግረኛ ፍልስጤማውያን ከተያዙ በኋላ አምስቱ ብቻ ነበሩ መድረስ የቻሉት።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ባለፈው መጋቢት ወር አሜሪካ መተላለፊያውን ለመገንባት 320 የአሜሪካን ዶላር ወጭ ማድረጓን እና 1000 ወታደሮች መሳተፋቸውን መናገራቸው ይታወሳል። ነገርገም አንድም የአሜሪካ ወታደር የጋዛን ምድር ስላለመለርገጡ ግለጽ አላደረጉም።
እስራኤል የሀማስ የመጨረሻ ምሽግ ይገኝባታል የምትላትን በግብጽ ድንበር የምትገኘውን የራፋ ከተማ እንዳታጠቃ ጫና ቢደረግባትም ሳትቀበለው ቀርታለች። እስራኤል ጋዛን በማጥቃቷ አጋሯን አሜሪካን ጭምር ቅር አሰኝታለች።
ሀማስ፣ አደራዳሪዎቹ ግብጽ እና ካታር ያቀረቡትን በሶስት ምዕራፍ የተከፋፈለ የተኩስ አቁም እቅድ ቢቀበልም፣ እስራኤል የምትፈልጋቸው ሁኔታዎች እንዳልተሟሉ በመግለጽ ሳትቀበለው ቀርታለች።
ይህን ተከትሎም ሀማስ ድርድሩ ወደ ሂደት ወደ ዜሮ ተመልሷል ሲል መግለጹ ይታወሳል።
አለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት(አይሲሲ) አቃቤ ህግ በጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ እንዲወጣ ጠይቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ የእስር ማዘዣ ጥያቄው የጸረ-ጽዮናዊነት ማቅጥቅጥ ማሳያ ነው ሲሉ ተቃውመውታል።