ተመድ 5.2 ሚሊዮን ሰዎች ከዲሞክራቲክ ኮንጎ መፈናቀላቸውን አስታወቀ
ዩኒሴፍ የሰብአዊ እርዳታ ለሚፈልጉት ህጻናት 384 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ብሏል
የተመድ ሪፖርት ከተፈናቀሉት መካከል 3 ሚሊዮን የሚሆኑት ህጻናት መሆናቸውን ጠቅሷል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዲሞክራቲክ ሪፐብክ (ዲ.አር) ኮንጎ 3 ሚሊዮን ህፃናትን ጨምሮ 5.2 ሚሊዮን ሰዎች መፈናቀላቸውን አስታውቋል፡፡ ተመድ እንደገለጸው ከተፈናቀሉት ግማሽ የሚሆኑት ሴቶች ባለፈት 12 ወራት በኃይል ቤታቸውን እንዲለቁ የተደረጉ ናቸው፡፡
የተመድ የህጻናት ፈንድ (ዩኒሴፍ) ከተፈናቀሉት ውስጥ 3 ሚሊዮን የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን ገልጿል፡፡
በምሰረቃዊ ጎንጎ አጥቂዎች ቆንጨራና ከባድ መሳሪያ በመጠቀም በፈጸሙት ምህረት የለሽ ጥቃት መንደሮች በጠቅላለ በእሳት ተቃጥለዋል፣ የጤና ጣቢያዎችና ትምህርት ቤቶች ተዘርፈዋል፤ሙሉ ቤተሰቦች ህፃናትን ጨምሮ ታንቀው ተገድለዋል ብሏል ዩኒሴፍ፡፡
የዩኒሴፍ የዲአር ተወካይ የሆኑት ኢድዋርዶ ቢግቤደር እንደተናገሩት የተፈናቀሉት ህጻናት ከፍርሃት፣ከርሃብና ጥቃት ውጭ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል፡፡አለም የህፃናቱ ስቃይ ያሳሰበው አይመስልም፤ህጻናቱ ጥሩ ራእይ እንዲኖራቸው መርዳት አለብን ብለዋል ተወካይዋ፡፡
ዩኒሴፍ የህዝቡ እርዳታ ለማድረግ ያለው ውስብስብነት እንደሚያሳስበው ገልጿል፤ እርዳታ የማድረስ ስራው በጸጥታ መደፍረስና በደካማ ትራንስፖርት መስተጓጎሉን ጠቅሷል፡፡
ዩኒሴፍ የሰብአዊ እርዳታ ለሚፈልጉት ህጻናት 384 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ እንደሚያስፈልግ አስታውቋል፡፡