የቀጣናው ኃይሎች ወደ ግጭት እጃቸውን ያስገባሉ ተብሎ ተሰግቷል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) በሱዳን በተነሳው ግጭት ሳቢያ 800ሺ የሚደርሱ ሱዳናውያን ሀገራቸውን ለቀው ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ገልጿል።
የሱዳን ተፋላሚ ጀነራሎች በአሜሪካ እና ሳኡዲ አረቢያ ጫና ተኩስ ለማቆም መስማማታቸውን ገልጸው የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ግጭቱ አገርሽቷል
በሱዳን በጀነራል አል ቡርሃን በሚመራው ጦር እና በጀነራል ሀምዳን ደጋሎ ወይም ሄሚቲ የሚመራው ጦር ግጭት ውስጥ ከገባ ሁለት ሳምንት ያለፈው ሲሆን በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለዋል።
ግጭቱ የሱዳንን ዋና ከተማ ካርቱምን የጦር ቀጣና ያደረገ ሲሆን የቀጣናው ኃይሎች ወደ ግጭት እጃቸውን ያስገባሉ ተብሎ ተሰግቷል።
ተመድ እንደገለጸው እስካሁን 73ሺ ሱዳናውያን ሀገራቸውን ለቀው ተሰደዋል።
ተፋላሚ ኃይሎቹ ግጭት አቁመው ወደ ንግግር እንዲመጡ የገለጸው ተመድ ሁለቱም ወገኖች ለመደራደር ዝግጁ አይደሉም ብሏል።
ግጭቱ ድንገት በመፈጠሩ እና ካርቱም ከተማ አየር መንገዱን ጨምሮ የጦር ሜዳ ስለሆነች የውጭ ዲኘሎማቶች ችግር ውስጥ ገብተው ነበር።
በርካታ ሀገራት ዜጎቻቸውን እና ዲፕሎማቶቻቸውን ከሱዳን ማስወጣት ችለዋል።