የሱዳን ግጭት በምን ሁኔታ ውስጥ ይገኛል፤ ምን አዲስ ነገር አለ?
የሱዳን ጦርነት እስካሁን የቀጠለ ሲሆን፤ በሁለቱም ወገኖች ጦርነቱን የማቆም ፍለጎት አላሳዩም
በጦርነቱ 528 ሰዎች ሲሞቱ፤ ከ4 ሺህ 500 በላይ ሰዎች ቆስለዋል
በሱዳን ጦር እና አር.ኤስ.ኤፍ ተብሎ በሚጠራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት ሶስተኛ ሳምንቱ ላይ ገብቷል።
በሱዳን ጦር ኃይሎችእና በፈጥኖ ደራሽ ሰራዊቱ (አርኤስኤፍ) መካከል ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ በሀገሪቱ ዋና ከተማ ካርቱም፣ አጎራባች በሆነችው ኦምዱርማን እና በሌሎችም አካባቢዎች ከባድ ውጊያ አለ።
ሶስተኛ ሳምንቱን በያዘው ግጭቱ ቢያንስ 528 ሰዎች ሲገደሉ፤ ከ4 ሽህ 500 በላይ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
የግጭቱ መንስኤ ምንድን ነው?
ግጭቱ እየተቀጣጠለ ያለው የጦሩ መሪ በሆኑት በጄኔራል አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን እና በተቀናቃኛቸው በጄኔራል መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) የስልጣን ሽኩቻ ነው።
ውጥረቱ የተፈጠረው ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ወደ ሀገሪቱ ጦር ኃይል ለማዋኻድ እና ይህን አሰራር ለመቆጣጠር የስልጣን ወሰን ላይ ነው።
የውህደቱ ሂደት በሱዳን የሽግግር ስምምነት ላይ የተገለጸ ወሳኝ መስፈርት ነው። እሱም በመጀመሪያ በፈረንጆች ሚያዝያ አንድ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም እስካሁን አልተፈረመም።
በሱዳን አሁን ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል?
የሱዳን ተዋጊ ኃይሎች በትናትናው እለት በድጋሚ የደረሱንትን የተኩስ አቁም ስምምነት መጣስን ተከትሎ ጣት እየተጠቋቆሙ ሲሆን፤ ደም አፋሳሹ ጦርነት ዛሬም ቀጥሏል።
ሶሰተኛ ሳምንቱን በያዘው ጦርነት አሁንም ከሁለቱ ወገኖች ጦርነቱን የማቆም ፍላጎት አላሳዩም የተባለ ሲሆን፤ በካርቱም እንዲሁም በዳርፉር ምእራባዊ ክፍል ላይ አዳዲስ ግጭቶች ተቀስቅሰዋል።
የሱዳን ጦር መሪ ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን፤ አር.ኤስ.ኤፍ ተብሎ በሚጠራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪ ጄነራል ሀምዳን ዳጋሎ ጋር መቼም ቢሆን ቁጭ ብዬ አልነጋገርም ማለታቸው ይታወቃል።
የአር.ኤስ.ኤፍ መሪ ጄነራል ሀምዳን ዳጋሎ ከዚህ ቀደም ከጄነራል አል ቡርሃ ጋር ከዚህ በኋላ መነጋገር ዋጋ የለውም ብለው የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ አል ቡርሃ ጦርነቱን ካቆመ የመነጋገር እድል ይኖራል ማለተቸው ተሰምቷል።