በሱዳን የተኩስ አቁም ስምምነቱ ተጥሶ ጦርነቱ ቀጥሏል
በሱዳን ጦር እና በጀነራል ሀምዳን ደጋሎ በሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት ሁለት ሳምንት ሆኖታል
በካርቱም ከባድ የጦር መሳሪያ ተኩስ እና የተጠመዱ ፈንጆች የመኖሪያ ሰፈሮች እያናወጡ ይገኛሉ
የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ለ72 ሰአታት የሚቆይ ተኩስ ለማቆም የተስማሙ ቢሆንም ስምምነቱ ተጥሶ ጦርነቱ ቀጥሏል።
በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም እና ከካርቱም ጎን የምትገኘው ባህሪ ከተማ የአየር ድብደባ፣ የተንክና ከባድ መሳሪያ ተኩስ እየናጣት ነው ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
በሱዳን ጦር እና በጀነራል ሀምዳን ደጋሎ በሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት ሁለት ሳምንት ሆኖታል።
ሁለት የጦር ጀነራሎች የሚመሩት የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ጦርነት ወስጥ በገቡበት ወቅት ተኩስ እንዲቆም ጥረት ቢደረግም አልተሳካም ነበር።
በቅርቡ በአሜሪካና ሳኡዲ አረቢያ አደራዳሪነት የተደረሰው ስምምነት ሲጀመር ተግባራዊ የነበረ ቢሆንም ይህም ስምምነት ተጥሶ ጦርነቱ ቀጥሏል።
በግጭቱ እስካሁን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል፤በርካታ ሰዎችም ቤት ንብረታቸውን ጥለው በመሸሽ ላይ ናቸው።
ይህ ጦርነት 10 አመት የሞላውን በምእራብ ዳርፉር የነበረውን ጦርነት የሚያስታውስ ነው።
በካርቱም ከባድ የጦር መሳሪያ ተኩስ እና የተጠመዱ ፈንጆች የመኖሪያ ሰፈሮች እያናወጡ ይገኛሉ።
ከባህሪ ከተማ ከፍተኛ ጭስ ሲወጣ ይታያል።
የተለያዩ ሀገራት በድንገት ጦርነት ውስጥ ከገባችው ሱዳን ዜጎቻቸውን አውጥተዋል፣አሁንም በማስወጣት ላይ ያሉ አሉ።
የሱዳን ጦር የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ይዞታዎችን ለመምታታ የሚያደረግው የአየር ጥቃት ስምሪት ነዋሪዎችን ችግር ውስጥ ከቷል።
ነዋሪዎቹ የምግብ፣ የውሃ እና የመብራት አቅርቦት በመቋረጡ ችግር ውስጥ ገብተዋል።
ተመድ ባወጣው ሪፖርት መሰረት 512 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን 4200 ሰዎች ደግሞ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል።