በአብየ ግዛት የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል የመተካቱ ሂደት በቀጣይ ወር ይጀመራል-ተመድ
የተመድ ሰላም አስከባሪ የላከው የሱዳንና የደበብ ሱዳን ጦሮች መፋጠጣቸውን ተከትሎ ነበር፡፡

ሱዳን በአብየ ያለው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር እንዲወጣ ጥያቄ አቅርባ፤ተመድም ጥያቄዋን መቀበሉ ይታወሳል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) የሰላም ማስከበር ዘመቻ ኃላፊ ጅን ፔሬ ላክሮክስ እንደገለጹት በአብየ ሚገኘውን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል የተመተካቱ ሂደት በቀጣይ ወር ይጀምራል፡፡
ሱዳን በአብየ ያለው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር እንዲወጣ ጥያቄ አቅርባ የነበረ ሲሆን ጥያቄዋም በተመድ ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል፡፡ ሱዳን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር ይወጣ ያለችው በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል በድንበር ጉዳይ አለመግባባት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ነው፡፡
- ሱዳን በአብዬ ግዛት ያለው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ለቆ እንዲወጣ ጠየቀች
- በአብዬ ግዛት የተሰማራው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር እንዲወጣ ያቀረበችውን ጥያቄ ተመድ እንደተቀበላት ሱዳን አስታወቀች
- በአብዬ ግዛት ያለው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሀይል የሚወጣ ከሆነ ለከፈለው መስዋዕትነት ክብር ተሰጥቶት ሊሆን ይገባል-ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ኃላፊዋ ላክሮክስ ይህን ያሉት ከሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ም/ቤት ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ጋር ባደረጉት የስልክ ወይይት ነው ተብሏል፡፡
የሽግግር ም/ቤቱ እንደገለጸው አልቡርሃን ከተመድ ኃላፊ ጋር ያደረጉት ውይይት የተመድ ኢንትሪም ሴኩሪቲ ፎርስ ፎረ አብየ ውስጥ ያሉት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮችን በሱዳን መንግስት በተጠየቀው መሰረት ለመተካት የመከረ ነበር፡፡
በስልክ ወይይቱ ወቅት ላክሮክስ የመተካቱና የመተካቱ ስራ በፈረንጆቹ ቀጣይ የካቲት ወር እንደሚጀመርና እስከ ፈረንጆቹ መጋቢት 2022 እንደሚገጥል ማረጋገጣቸው ተዘግቧል፡፡
የተመድ የጸጥታው ም/ቤት ሰላም አስከባሪ ወደ አብየ ግዛት የሰላም አስካሪ የላከው፤ በነዳጅ በበለጸገችው አብየ ግዛት የሱዳንና የደበብ ሱዳን ጦሮች መፋጠጣቸውን ተከትሎ ነበር፡፡