በየመን በተመድ አማካኝነት የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ለ2 ወራት ተራዘመ
ተኩስ አቁም ቢደረግም በመንግስት ቁጥጥር ስር ያለቸው ከተማ አሁንም በከበባ ውስጥ ነች
በየመን ተፋላሚ ወገኖች መካከል በሚያዚያ ወር ተደርሶ የነበረው ስምምነት ለ2 ወራት መራዘሙን ተመድ ገለጸ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) የመን ልዩ መልዕክተኛ ሃንስ ግሩንድበርግ ሐሙስ ዕለት እንዳስታወቁት የየመን ተፋላሚ ወገኖች የተጀመረውን የተኩስ አቁም ስምምነት ለተጨማሪ ሁለት ወራት ለማራዘም መስማማታቸውን አስታውቀዋል።
ግሩንድበርግ በተመድ ድረ-ገጽ ላይ በጽሁፍ ባወጡት መግለጫ ስምምነት የሚራዘመው እና ተግባራዊ የሚሆነው ስምምነቱ የተደረሰበት ጊዜ ዛሬ ባለቁን ተከትሎ ነው፡፡
የግሩንድበርግ መግለጫ ባለፉት ወራት ከየመን ተፋላሚ ወገኖች ተወካዮች እና ከከፍተኛ ፖለቲከኞች ጋር ተከታታይ ስብሰባዎችን ካደረገ በኋላ በታላቁ የረመዳን ወር የመጀመሪያ ቀን የተጀመረው እና በመጪው ሀሙስ የሚጠናቀቀው ሀገር አቀፍ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲቀጥል ለማድረግ ነው።
"ባለፉት ሁለት ወራት የየመን ዜጎች የተኩስ አቁሙን ጥቅሞች አይተረዋል፡፡ በሲቪሎች ላይ የሚደርሰው ጉዳት በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል፣ በሆዴዳ ወደብ በኩል ያለው የነዳጅ አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፣ የንግድ በረራዎችም ወደ ሰነዓ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ እና ወደ ስድስት ዓመታት ያህል ከተዘጉ በኋላ ቀጥለዋል” ሲል የተመድ ልዩ መልእክተኛው ተናግረዋል፡፡
የተመድ ልዑክ በመግለጫው እንዳስታወቀው በታይዝ ላይ ያለውን ከበባ ለማንሳት ድርድር እየተካሄደ ነው።አክለውም“እርቁን ተግባራዊ ለማድረግ እና አሁን ለማደስ በመስማማት ፓርቲዎቹ ለየመናውያን ይህን አውዳሚ ግጭት ማስቆም ይቻላል የሚል ብርቅ ጭላንጭል ተስፋ ሰጥተዋል።”
በተመድ አማካኝነት በየመን ያሉ ተፋላ ወገኖች በሚያዚያ ወር ለ2 ወራት የሚቆይ ተኩስ አቁም ያካሄዱ ሲሆን ይህም የንግድ በረራዎች በሃውቲ ቁጥጥር ስር በሚገኘው ሰነዓ እና የነዳጅ መርከቦችን በሃውቲ ወደተያዘው የሆዴዳ ወደብ እንዲገቡ መፍቀድ እና የግዛቱን ጉዞ ማንሳትን ይጨምራል።
ስምምነቱ በመንግስት ቁጥጥር ስር ያለችውን የታይዝ ከተማ ከበባም ማንሳትም ይጨምር ነበር፡፡
ተፋላሚዎቹ ወገኖች በተኩስ አቁሙ ስምምነት በአብዛኛው ቢገዙም፤የታይዝ ከተማን ከበባ ለማንሳት የመጨረሻ ስምምነት ላይ ሊደርሱ አልቻሉም።
በ2014 መገባደጃ ላይ በኢራን የሚደገፈው የሃውቲ ሚሊሻ በርካታ ሰሜናዊ ግዛቶችን ከተቆጣጠረ እና በሳዑዲ የሚደገፈውን የየመን መንግስት ከዋና ከተማይቱ ሰነዓ ካስወጣ በኋላ በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ትገኛለች።ጦርነቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድሏል፣ 4 ሚሊዮን ተፈናቅሏል፣ ሀገሪቱን ወደ ረሃብ አፋፍ አድርጓታል።