ዩክሬን በደረሰባት ወታደራዊ እርምጃም ማገገም ከማትችልበት ደረጃ ላይ መድረሷንም ሩሲያ ገልጻለች
ሩሲያ ከ23 ሺህ በላይ የዩክሬን ወታደሮች መግደሏን ገለጸች፡፡
ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ በሚል ከሩሲያ ጋር ጦርነት ከተጀመረ ከ50 ቀን በላይ ሆኖታል፡፡
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሜጀር ጀነራል ኢጎር ኮናሼንኮቭ እንዳሉት አገራቸው በዩክሬን በጀመሩት ልዩ ዘመቻ ከ23 ሺህ በላይ ወታደሮች መገደላቸውን ገልጸዋል፡፡
ከአንድ ሺህ በላይ የዩክሬን ባህር ኃይል አባላት እጅ መስጠታቸውን ሩሲያ ገለጸች
የሩሲያ ወታደሮች በዩክሬን እያካሄዱት ባለው ልዩ ዘመቻ የዩክሬን ጦር፣ ብሄራዊ ዘብ እና ቅጥረኛ ወታደሮችን መግደላቸውን እና መማረካቸውን ቃል አቀባዩ አክለዋል፡፡
ዩክሬን ከደረሰባት ወታደራዊ እርምጃ ማገገም በማትችልበት ደረጃ ላይ ደርሳለች ያለችው ሩሲያ በዩክሬኗ ማሪዮፖል የወደብ ከተማ ከ4 ሺህ በላይ ወታደሮች መግደሏን አክላለች፡፡
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘለንኪ በሩሲያ ጦር የደረሰባቸውን ሽንፈት ለህዝባቸው ለመንገር አፍረዋል ሲሉም የሩሲያ ጦር ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡
ሩሲያ በዩክሬን እያካሄደች ባለው ልዩ ዘመቻ የፈጸመቻቸውን ድሎች እና በዩክሬን ላይ ያደረሰቻቸውን ጉዳቶች ሙሉ ሪፖርት በቅርቡ ለህዝብ ይፋ እንደምታደርግም ቃል አቀባዩ ገልጸዋል፡፡
የዩክሬን ፕሬዝዳንት በአፍሪካ ህብረት ንግግር ለማድረግ ጠየቁ
ዩክሬን በበኩሏ ከሩሲያ ጋር እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሁለት ሺህ እስከ ሶስት ሺህ ወታደሮች እንደተገደሉባት ገልጻ በአንጻሩ ግን 20 ሺህ የሩሲያ ወታደሮችን እንደገደለች ለሲኤንኤን ተናግረዋል፡፡
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ግን ከዩክሬን የተሰማውን ዜና ውድቅ አድርጎ በዩክሬን ምድር እየተካሄደ ባለው ልዩ ዘመቻ የተገደሉ ወታደሮች ብዛት ከ2 ሺህ ያነሰ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ሩሲያ አክላም ምዕራባዊያን አገራ ለዩክሬን የለገሷቸው ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን ማውደሟን ገልጻ ምዕራባዊያን አገራት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እና የጦር መሳሪያዎቹ በሚያርፉባቸው ቦታዎች ሁሉ ተከታትላ እርምጃ እንደምታወድማቸው አስጠንቅቃለች፡፡