ተመድ ቻይና የጸረ- ሽብር ፖሊሲዎቿን እንድትገመግም ማሳሰቡን አስታወቀ
ባችሌት በቻይና ያልተጠበቀ ጉብኝት ቢያደርጉም ጉብኝታቸው በምዕራባውያን ዘንዳ ቅሬታ ፈጥረዋል
የቻይና መንግስት ከምዕራባውያን እና ሰብዓዊ መብቶች ተቋማት የሚነሱ ክሶች እንደማይቀበላቸው አስታውቋል
የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ኃላፊ ሚሼል ባችሌት ቻይና የጸረ-ሽብር ፖሊሲዎቿን እንድትገመግም ማሳሰባቸው አስታወቁ፡፡
ባችሌት ይህንን ያሉት በቅርቡ በቻይና ያደረጉት ጉብኘረት ተከትሎ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ተቋማትና ምዕራባውያን ትችት በማስተናገዳቸው ነው፡፡
በዚህም ባችሌት ለተቺዎቻቸው በሰጡት ምልሽ “ግድ የላችሁም ቤጂንግ የጸረ- ሽብር ፖሊሲዎቿን እንድትገመግምና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት መስፈርቶችን ያሟሉ መሆናቸውን እንድታረጋግጥ አስስቤያታለሁ” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ባችሌት በቻይና ምዕራባዊው ከፍል በምትገኘውና የበርካቶች ማጎርያና የሲቃይ ማእከል እንደሆነች በሚነገርላት የዢንጂያንግ ግዛት ያደረጉት የስድስት ቀናት ጉብኝት፤ ከሀገሪቱ መንግስት ጋር የመገናኘት እድል የፈጠረ ጥሩ አጋጣሚ እንደነበርም ገልጿል፡፡
ባችሌት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፡ በቻይና ቆይታየ “የፀረ-ሽብርተኝነት ፖሊሲን እና የጥላቻ እርምጃዎችን አተገባበር በተመለከተ ያሉኝን ጥያቄዎችን እና ስጋቶችን አንስቻለሁ ፣በተለይም በኡዩጉሮች እና በሌሎች አናሳ ሙስሊም ወገኖች መብት ላይ ስላለው ተፅእኖ አንስቻለሁ” ብለዋል፡፡
ይሁን እንጂ የቻይና መንግስት ከሰብዓዊ መብቶች ተቋማት የሚነሱ ክሶች እንደማይቀበላቸው አስታውቋል፡፡
የባችሌት ጉብኝት አንድ የተመድ ከፍተኛ የስብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ቻይና ሲጎበኙ ከ17 ዓመታት የመጀመርያው መሆኑ ነው፡፡
ያም ሆኖ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች እና ምዕራባውያን ሀገራት የባችሌት ጉዞ በቻይና የመብት ጭላንጭል እንዳለ ማሳያ አድርጋ ለማስረጃነት ልትጠቀምበት ትችላለች የሚል ነገር ያስጨነቃቸው ይመስላል፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ "በእንዲህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ለመጎብኘት መስማማት ስህተት ነው" ብለዋል፡፡
ቻይና መጀመሪያ ላይ በዢንጂያንግ ውስጥ ምንም ዓይነት የማቆያ ካምፖች የለም ብላ የነበር ቢሆንም፤ በ2018 ግን በግዛቱ ሽብርተኝነትን እና የሃይማኖት አክራሪነትን ለመግታት አስፈላጊ ናቸው ያለቻቸው "የሙያ ማሰልጠኛ" በሚል የተለያዩ መእከላት አቋቁማለች፡፡
ይሁን እንጂ ማእከላቱ በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሚካሄዱባቸው ካምፖች እንደሆኑ በተለያዩ ጊዜያት ይነገራል፡፡
በዚህም ባቼሌት በማዕከላቱ አሰራር ላይ ገለልተኛ የዳኝነት ቁጥጥር አለመኖሩን እና የኃይል አጠቃቀምን ፣ እንግልትን እና በሃይማኖታዊ ድርጊቶች ላይ ከባድ ገደቦች መኖራቸው እጅጉ እንደሚያሳስባቸው ለቻይና መንግስት መናገራቸው ገልጿል፡፡