የሱዳን ወታደራዊ ኃይል መሪ “ተቃውሞ በሚያሰሙ ዜጎች ላይ የኃይል እርምጃ እንዳይወስዱ”ተመድ አሳሰበ
በሱዳን የተመድ ልዩ መልዕክተኛ ቮልከር ፓርተስ “ከሱዳኑ ሁለተኛው ሰው ጀነራል ዳግሎ” ጋር ተገናኝተው መክረዋል
በሚሊየን የሚቆጠሩ ሱዳናውያን አደባባይ ወጥተው ተቃሟቸውን በማሰማት ላይ ናቸው
የሱዳን ወታደራዊ ኃይል መሪ ተቃውሞ በሚያሰሙ ዜጎች ላይ በሚወስዱት የኃይል እርምጃ እንዲጠነቀቁ ተመድ አሳሰበ፡፡
በሱዳን የተባበሩት መንግስታት ልዩ መልዕክተኛ ቮልከር ፓርተስ ለሱዳኑ መሪ ሌ/ጀነራል አብደል ፋታህ አል-ሲሲ ቅርብ እንደሆኑ የሚነግርላቸውና የመፈንቅለ መንግስቱ ዋና መሪ ጀነራል ሞሃመድ ሃምዳን ዳግሎን አግኝተው በወቅታዊ የሱዳን ሁኔት ዙርያ መምከራቸው ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ልዩ መልዕክተኛው ከዳግሎ ጋር በነበራቸው ቆይታ ወታደራዊ መሪዎቹ “ዜጎች ተቃውሞአቸውን በሰላማዊ መንገድ የሚገልጹበት ሁኔታ እንዲያመቻችኑና አላስፈላጊ እርምጃ ከመውስድ እንዲቆጠቡ” አሳስቧል፡፡
የዴሞክራሲ አቀንቃኞች ነን የሚሉ የሱዳን አክቲቪስቶች “የፈረሰው የሽግግር መንግስት ወደነበረበት እንዲመለስ እና ከፍተኛ የፖለቲካ ባለስልጣናትን ከእስር እንዲፈቱ” የሚል ዓላማ ያለው ሰልፍ በዛሬው ዕለት እንዲካሄድ “በሚልዮኖች ለሚቆጠሩ ዜጎች” ጥሪ ማቅረባቸው ይታወቃል።
በዚህም መሰረት በዛሬው እለት የሱዳን ጦር በሲቪል አስተዳደሩ ላይ የወሰደውን እርምጃ በመቃወም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሱዳናውያን አደባባይ ወጥተው ተቃውሞአቸው በማሰማት ላይ ናቸው።
አሜሪካ እና ብሪታንያ የሱዳን የፀጥታ ሀይሎች ተቃውሞዋቸውን በሰላማዊ መንገድ ለማሰማት አደባባይ በሚወጡ ዜጎች ላይ የሀይል እርምጃ እንዳይወስዱ አስጠንቅቋል።
ባሳለፍነው ሰኞ ሱዳን ጦር ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ እና የካቢኔ አባሎች በማስር ስልጣኑን መቆጣጠራው ይታወሳል።
በጦሩ እርምጃ የተናደዱት በርካታ ሱዳናውያን ወደ ካርቱም አደባባይ በመውጣት ተቃውሞ ማሰማት የጀመሩ ሲሆን፤የተቃውሞ ሰልፎቹን ወደ አመፅ መለወጣቸውን ተከትሎ የፀጥታ ሀይሎች በወሰዱት እርምጃ የ7 ሰዎች ህይወት ማለፉን ከ140 ሰዎች በላይ መቁሰላቸው ይታወሳል፡፡