“ሃምዶክ አሁንም፤ ሱዳንን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ለመምራት የመጀመሪያ እጩ ናቸው”- አል ቡርሃን
በስምምነት የሚመረጠው ጠቅላይ ሚኒስትር ያለ ጦሩ ጣልቃ ገብነት መንግስት እንደሚያዋቅርም ነው ቡርሃን የተናገሩት
ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን በሙያተኞች (technocrat) የሚመራ መንግስት ይቋቋማል ብለዋል
በሙያተኞች (technocrat) የሚመራ መንግስትን ለማቋቋም እንደሚሰሩ የሱዳን ጦር መሪ ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ተናገሩ፡፡
መንግስት ሊመሰርት የሚችለው ጠቅላይ ሚኒስትር በጦሩ ስምምነት ይመረጣል ያሉት ቡርሃን ተመራጩ ጠቅላይ ሚኒስትር ያለ ጦሩ ጣልቃ ገብነት መንግስት እንደሚያዋቅር ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ፤ በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ የአፍሪካ ህብረት ውሳኔን እንደምታከብር ገለጸች
“የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በፖለቲካ እና በጦሩ ስምምነት ነበር የተመረጠው፡፡ አሁን ግን የፖለቲካ ኃይሎቹ የሉም፡፡ በመሆኑም ህዝቡን እስከ ምርጫ ድረስ የመምራት ኃላፊነት ይኖርብናል፡፡ ከተማሩት መካከልም ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንመርጣለን” ሲሉ ለሩሲያው ስፑትኒክ የተናገሩት፡፡
ሆኖም እነ ማን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት እጩ ሆነው እንደቀረቡና እንደሚወዳደሩ አልገለጹም፡፡
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ሉዓላዊ ምክር ቤቱ በቀናት ውስጥ ቢበዛ በሳምንት ውስጥ ይፋ እንደሚደረጉም ገልጸዋል፡፡
አል ዐይን አረብኛ ግን አብደላ ሃምዶክ ለጠቅላይ ሚኒስትርነቱ ቀዳሚው እጩ መሆናቸውን ቡርሃንን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡
ሃምዶክ፤ በቡርሃን የሚመራው ጦር የሽግግር መንግስቱን ከማፍረሱ በፊት የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ፡፡
አሁንም ሃምዶክ “ራሳቸውን ካልቆጠቡ በስተቀር ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ከሚታሰቡት እጩዎች ቀዳሚው ናቸው” ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ገለጻ፡፡
በሽግግሩ የታዩ ክፍተቶችን ለማረም የተወሰዱ “የእርምት እርምጃዎች ሊቀጥሉ አልቻሉም” በሚል ከሃምዶክ ጋር ቀደም ሲልም ተስማምተን ነበር የሚሉት ቡርሃን ስምምነታቸው በሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት ምክንያት መበላሸቱን ተናግረዋል፡፡
ሆኖም “ሶስተኛ” የተባሉት እና በጣልቃ ገብነት የተጠቀሱት አካላት እነ ማን እንደሆኑ አልገለጹም፡፡
ከአፍሪካ ህብረት የታገደችው ሱዳን በግድቡ የድርድር ሂደት አትሳተፍም ተባለ
“በእርምት እርምጃዎቹ የሱዳናውያንን የተመረጠ የሲቪል መንግስት ፍላጎት ከማሟላት ውጭ ሌሎች የበስተጀርባ ፍላጎቶች የሉንም” ሲሉም ነው የሚያስቀምጡት፡፡
“ሃምዶክ አሁንም ራሳቸውን ካልቆጠቡ በስተቀር ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የመጀመሪያ እጩ ናቸው”ሲሉም አክለዋል ሌተናል ጄነራሉ፡፡
ጠቅላይ የጦር አዛዡ “ጦሩ የሃገሪቱን ህገ መንግስት አግዷል” መባሉን ያስተባበሉም ሲሆን “ቃላችንን እንፈጽማለን፤ ማንም ፍላጎቱን በህዝብ ላይ አይጭንም”ሲሉ መልሰዋል፡፡