ተመድ 'በሽብር' ተግባር ተሳትፈዋል የተባሉ ሰራተኞቹን እንደሚቀጣ አስታወቀ
ብሪታንያ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ኔዘርላንድስ፣ ስዊዘርላንድ እና ፊንላንድ ለኤጀንሲው እርዳታ ያቆሙትን ካናዳ እና አሜሪካን በትናንትናው እለት ተቀላቅለዋል
ዋና ጸኃፊው እነዚህን ግለሰቦች ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ፣ ተመድ ለመተባበር ዝግድ ነው ብለዋል
ተመድ 'በሽብር' ተግባር ተሳትፈዋል የተባሉ ሰራተኞቹን እንደሚቀጣ አስታወቀ።
የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ "በሽብር ተግባር የተሰማራ ማንኛውም ሰራተኛ" ቅጣት ይጠብቀዋል ሲሉ ዝተዋል።
ዋና ጸኃፊው ይህን ያሉት እስራኤል የተወሰኑ የተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ ሰራተኞች ሀማስ ባለው አመት ጥቅምት ወር በእስራኤል ላይ ባደረሰው ጥቃት ተሳትፈዋል የሚል ክስ ማቅረቧን ተከትሎ ነው።
ከዚህ ክስ በኋላ በርካታ ሀገራት ለተመድ የስድተኞች ኤጀንሲ ለፍስጤማውያን (ዩኤንአርደብሊውኤ) የሚያውለውን ድጋፍ አቁመዋል።
ነገርግን ጉተሬዝ ሀገራት ለፍለስጤማውያን የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲቀጥሉ ተማጽነዋል።
ጉተሬዝ ባወጡት መግለጫ " በሽብር ድርጊት የተሳተፈ ማንኛውም የተመድ ሰራተኛ በወንጀል ጭምር ይጠየቃል" ብለዋል።
ዋና ጸኃፊው እንደገለጹት በተመድ መደበኛ አስራር መሰረት እነዚህን ግለሰቦች ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ፣ ተመድ ለመተባበር ዝግድ ነው።
ጉተሬዝ አክለውም በተመድ የስደተኞች ድርጅት ስር ሆነው በፍልስጤም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚሰሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መቀጣት የለባቸውም ብለዋል።
ብሪታንያ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ኔዘርላንድስ፣ ስዊዘርላንድ እና ፊንላንድ ለኤጀንሲው እርዳታ ያቆሙትን ካናዳ እና አሜሪካን በትናንትናው እለት ተቀላቅለዋል።
ሀገራቱ በጋዛ ለሚኖሩ ፍልስጤማውያን አስፈላጊ የሚባሉ እርዳታዎችን ያደርጉ ነበር።