ሊባኖስ ሌላኛዋ ጋዛ እንዳትሆን የተመድ ዋና ጸኃፊ አስጠነቀቁ
በተመድ የኢራን ተልእኮ ሄዝቦላ ራሱን እና ሊባኖስን ከእስራኤል ጥቃት የመከላከል አቅም አለው ሲል በትናንትናው እለት ተናግሯል
የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በእስራኤል እና ሄዝቦላ ያለው ውጥት መካረር እንዳስጨነቃቸው በትናንትናው እለት ተናግረዋል
ሊባኖስ ሌላኛዋ ጋዛ እንዳትሆን የተመድ ዋና ጸኃፊ አስጠነቀቁ።
የተባበሩት መንግስት ድርጅት(ተመድ) ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በእስራኤል እና ሄዝቦላ ያለው ውጥት መካረር እንዳስጨነቃቸው በትናንትናው እለት ተናግረዋል።
"አንድ ችኩል እርምጃ ወይም የተሳሳተ ስሌት ከምናስበው በላይ ድንበር ተሻጋሪ አስከፊ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል" ሲሉ ጉተሬዝ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
"ግልጽ እንሁን። የቀጣናው ህዝብ እና የዓለም ህዝብ ሌባኖስ ሌላኛዋ ጋዛ እንድትሆን አይፈልግም።"
በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላ ባለፈው ጥር ወር የእስራኤል-ሀማስ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ለሀማሰ አጋርነት ለማሳየት ወደ እስራኤል በርካታ ሚሳይሎችን አስወንጭፏል፤ በዚህም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ እስራኤላውያን ከቤታቸው ተፈናቅለዋል።
በዚህ ምክንያት እስራኤል በሄዝቦላ ላይ ጠንካራ እርምጃ እንድትወስድ የፖለቲካ ጫና እየተፈጠረባት ነው።
እስራኤልም በደቡብ እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሊባኖሳውያን ተፈናቅለዋል።
በተመድ የኢራን ተልእኮ ሄዝቦላ ራሱን እና ሊባኖስን ከእስራኤል ጥቃት የመከላከል አቅም አለው ሲል በትናንትናው እለት ተናግሯል።
"ማንኛውም ጥንቃቄ የጎደለው የእስራኤል ወረራ ቀጣናውን ወደ አዲስ ጦርነት ያስገባዋል" ብሏል ተልእኮው በኤክስ ገጹ ባወጣው መግለጫ።
የተመድ የሰላም አስከባሪ እና ያልታጠቁ የቴክኒክ ተቆጣጣሪዎች በእስራኤል እና ሊባኖስ ድንበር አካባቢ ያሉ ትንኮሳዎችን ለመከታተል ከሰፈሩ ረጅም ጊዜ ተቆጥሯል።
"በመሬት ላይ ያሉት የተመድ ሰላም አስከባሪዎች ውጥረቱን ለማርገብ እና የተሳሳቱ እርምጃዎችን ለመከላከል እየሰሩ ነው"ሲሉ ጉተሬዝ ተናግረዋል።
"ወታራዊ መፍትሄ መኖር የለበትም" ያሉት ጉተሬዝ አለም ውጥረቱ እንዲረግብ ድምጹን ማሰማት አለበት ብለዋል።