የብድር ጫና ምንድነው?
በፋይናንስ አለም ውስጥ 'የብድር ጫና' የሚለው ቃል ትኩረት የሚስብ ርዕስ ነው
የብድር ጫና በግለሰብ፣ በኩባንያዎች ወይም በመንግስት ላይ ተጽእኖ የሚያሳድር ሲሆን የፋይናንስ ስርአትን መረጋጋት እና ትርፋማነትን ይወስናል
የብድር ጫና ምንድነው?
በፋይናንስ አለም ውስጥ 'የብድር ጫና' የሚለው ቃል ትኩረት የሚስብ ርዕስ ነው። የብድር ጫና በግለሰብ፣ በኩባንያዎች ወይም በመንግስት ላይ ተጽእኖ የሚያሳድር ሲሆን የፋይናንስ ስርአትን መረጋጋት እና ትርፋማነትን ይወስናል።በዚህ ጽሁፍ የብድር ጫና ምን ያስከትላል፤ እንዴት ይከሰታል እና ሊያመጣ ስለሚችለው አሉታዊ ተጽዕኖ እንመለከታለን።
የብድር ጫና ማለት የተጠራቀመ ብድር የሚያመጣው ችግር ማለት ነው። ኩባንያ፣ ግለሰብ ወይም መንግስት ካላቸው ሀብት ወይም ገቢ ጋር የተመጣጠነ ብድር መበደራቸውን መቆጣጠር ኃላፊነት የሚጠይቅ ተግባር መሆኑ ግለጽ ነው።
የቤት ብድር፣ የትምህርት ቤት ክፍያ እና የግል ብድሮች መደራረብ በግለሰብ ላይ የብድር ጫና ያስከትላሉ። ብድር ኢንቨስትመንትን ለመጨመር የሚረዳ ቢሆንም ከመጠን ያለፈ ብድር ጭንቅት ያመጣል። ከፍተኛ የሆነ ወርሃዊ የብድር ክፍያ በጀትን ያቃውሳል፤ ለወደፊት ለሚደረግ ቁጠባ እንቅፋት ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪም አዲስ ብድር የማግኘት እድልን ይገድባል።
በተመሳሳይ ኩባንያዎችም የብድር ጫና ያጋጥማቸዋል። ኩባንያዎች ብዙ ስራቸውን ለማከናወን እና ለማስፋፋት ብድር ወደመጠቀም ያመራሉ። ነገርግን ብድር ለመመለስ በቂ ገንዘብ ሳይኖር የሚደረግ ብድር ችግር ውስጥ ይከታቸዋል። ከፍተኛ የብድር ክፍያ ትርፍን የሚቀንስና ሰራውን ወደ ኪሳራ የመዳረግ ችግር ያስከትላል።
የብድር ጫና ግለሰብን እና ኩባንያዎችን ብቻ የሚፈትን አይደለም። መንግስትም እንዲሁ በብድር ጫና ችግር ውስጥ የሚገባበት ብዙ አጋጣሚ አለ። መንግስታት ብዙ ጊዜ የሚበደሩት የተለያዩ ኘሮጀክቶችን ለማሰራት፣ የኢኮኖሚ እድገት ለማነቃቃት እና የበጀት ጉድለትን ለመሙላት በማለም ነው። የብድር ከጠቅላላ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ገቢ ጋር ያለው ምጥነት የመንግስታትን የብድር ጫና ለመለካት እንደመስፈርት ያገለግላል።
ምጥነቱ ከፍተኛ በሚሆንበት ጊዜ መንግስት ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ሀብት አንጻር ከፍ ያለ ብድር እንደወሰደ የሚያሳይ ሲሆን ያልተረጋጋ የገንዘብ ስርአት ያስከትላል። ከዚህ በጨማሪም መንግስት ከፍተኛ ወለድ ያለው ብድር ለመክፈል እና አስፈላጊ ፖሊሲዎችን እንዳያስፈጽም እክል ያጋጥመዋል።
የብድር ጫና የሚያስከትለው ጉዳት ለረጅም ጊዜ የሚቆይ እና ከባድ ነው። ግለሰቦች የብድር ኡደት ውስጥ እንዲገቡ እና ከብድር ለመውጣት ከባድ ያደርግባቸዋል። ኩባንያዎችም ከመጠን በላይ የሆነ ብድር ከተበደሩ በገበያ ተወዳዳሪነታቸው እና የማደግ እና የማስፋፋት እቅዳቸውን ይገታል።
መንግስትም የብድር ጫና ሰለባ ይሆናል። ያልተረጋጋ የብድር ጫና መንግስት አስፈላጊ የሆኑ የህዝብ ልማቶችን እንዳያሟላ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን እንዳይፈታ እንቅፋት ይሆንበታል። ከፍተኛ የብድር መጠን ከፍተኛ የሆነ የወለድ መጠን ስለሚያስከትል አስፈላጊ የሆኑ የህዝብ ፍላጎቶችን ለማሟላት ስለሚያስቸግር በዜጎች ደህንነት ላይ ችግር ያመጣል።
የብድር ጫና አሉታው ተጽዕኖ ለመከላከል በኃላፊነት መበደር እና ጥሩ የሆነ የፋይናንስ አስተዳደር ያስፈልጋል።
የብድር ጫና እንዳይከሰት መንግስት የተረጋጋ የብድር ስርአትን የሚደግፍ እና ወጭዎች በአግባቡ የሚቆጣጠር ኃላፊነት ያለው የበጀት ፖሊሲ አስፈላጊ ሊኖረዎ ይገባል።