በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ሳይፈነዳ የቀረ ቦንብ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አፈናቀለ
250 ኪሎ ግራም ይመዝናል የተባለው ይህ ቦንብ የተገኘው በደቡባዊ ፖላንድ ከተማ በባቡር ማቋረጫ መስመር አቅራቢያ ነው
የፖላንድ ጦር ቦንቡ ጀርመን 2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የተጠቀመችበት ከአየር የሚተኮስ ነው ብሏል
በ2ኛው የዓለም ጦርነት የዓለም ጦርነት ወቅት ሳይፈነዳ የቀረ ቦንብ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቀያቸው እንዲፈናቁሉ አስገድዷል።
- በአውሮፓው ድርቅ የውሃ መጠን በመቀነሱ በ2ኛው የአለምጦርነት ወቅት የነበሩ የጦር መርከቦች ብቅ አሉ
- ዓለም ከ2ኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ታይቶ በማይታወቅ ምጣኔ ሃብታዊ ልሽቀት ውስጥ ትገኛለች- የዓለም ባንክ
ይህ ያልፈነዳ ግዙፍ ቦንብ የተገኘው በፖላንዷ ሮክሎው ከተማ ሲሆን 2500ሰዎች እንዲፈናቀሉ ምክንያት መሆኑን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።
250 ኪሎ ግራም ይመዝናል የተባለው ይህ ቦንብ የተገኘው በደቡባዊ ፖላንድ ከተማ በባቡር ማቋረጫ መስመር አቅራቢያ ነው።
ቦንቡ ሊገኝ የቻለው በግንባታ ስራ ላይ በነበሩ ሰዎች ነው።
የፖላንድ ጦር ቦንቡ ጀርመን 2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የተጠቀመችበት ከአየር የሚተኮስ ነው ብሏል።
ባለሙያዎች ቦንቡን በሚያስወግዱበት ወቅት ችግር እንዳይከሰት የተማዋ ነዋሪዎች ወደ ሌላ ቦታ ለመውሰድ ትራንስፖርት እያመቻቸች መሆኑም ተገልጿል።
በዚሁ ምክንያት የባቡር እንቅስቃሴም እንዲቆም ተደርጓል።
ሮክላው በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ከባድ ጦርነት የተካሄደባት የጀርመን ከተማ ነበረች።
በጀርመን ሽንፈት ካበቃው ጦርነት በኋላ ድንበሮች በድጋሚ ሰሲመሩ ከተማ ወደ ፖላንድ ልትካለል ችላለች።