ልክ እንደተነሳ ለማረፍ ወሳኝ የሆነ ጎማው የወደቀበት የዩናትድ ኤርላይንስ አውሮፕላን መጨረሻ እንዴት ሆነ?
የዩናትድ ኤርላይንስ ቦይንግ 757-200 አውሮፕላን ልክ እንደተነሳ ጎማው ወድቆበታል
ቦይንግ አውሮፕላን ከዚህ ቀደም በበረራ ላይ የሞተር ሽፋንና መስኮት መገንጠል አደጋዎች አጋጥመውት ነበር
ንብረትነቱ የዩናትድ ኤርላይንስ ቦይንግ 757-200 አውሮፕላን ልክ እንደተነሳ ለማረፍ ወሳኝ የሆነው ጎማው አየር ላይ እንደወደቀበት ተነግሯል።
አውሮፕላኑ በትናንትናው እለት ከአሜሪካዋ ሎስ አንጀለስ በተነሳበት ወቅት ጎማው ተገንጥሎ መውደቁን ነው ዩናትድ ኤርላይንስ ያስታወቀው።
በረራ ቁጥሩ ዩናትድ 1001 የሆነው ቦይንግ 757-200 አውሮፕላን ያለ ምንም ችግር ዴንቨር በሰላም ማረፉንም ነው አየር መንገዱ ያስታወቀው።
የዩናትድ ኤርላይንስ በአደጋው ዙሪያ በሰጠው ማብራሪያ፤ “የአደጋውን መንስኤ እየመረመርን ነው” ብሏል።
በአውሮፕላኑ ላይ ይሆን በመሬት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩንም ነው የአር መንገዱ ያስታወቀው።
ቦይንግ ኩባንያ በጉዳዩ ላይ በኢ-ሜይል በሰጠው ምላሽ “የቦይንግ 757 አውሮፕላን ምርትን በፈረንጆቹ 2004 ላይ እንዳቆመ አስታውቋል።
ባሳለፍነው መጋቢት ወር ላይ ቦይንግ B777-200 ጄት አውሮፕን ከአሜሪካዋ ሳንፍራንሲስኮ ከተነሳ በኋላ አየር ላይ ጎማ የመውደቅ አደጋ አንዳጋጠመው ይታወሳል።
በተጨማሪም ቦይንግ አውሮፕላን ከዚህ ቀደም በበረራ ላይ የሞተር ሽፋንና መስኮት መገንጠል አደጋዎች አጋጥመውት እንደነበረ አይዘነጋም።
ከዚህ ጊዜ በኋላ ተደጋጋሚ የምርት ጥራት ችግሮች የተከሰቱ ሲሆን የአሜሪካ አቪዬሽን አስተዳድር በኩባንያው ላይ የቴክኒክ ጥራት ምርመራዎችን አድርጓል።
ኩባንያው በቦይንግ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን ምርቶች ላይ ካከናወናቸው 89 የጥራት ምርመራዎች ላይ በ33ቱ ጉድለት እንደተገኘበት መገለጹም ይታወሳል።
ይህ አውሮፕላን በተለይም የኤሮ ሲስተሙ ሲፈተሸ የጥራት ደረጃውን ያሟላው ከ13 ነጥቦች በስድስቱ ብቻ አልፏል ተብሏል።
የኩባንያው የቴክኒክ ባለሙያዎች ስለ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን በቂ እውቀት እንዳላቸው በተደረገው ምርመራ የሚገባውን ያህል ያውቃሉ የሚለውን ኩባንያው ማስረዳት እንዳልቻለም ተገልጿል።