በእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት የተከሰቱ አዳዲስ ሁነቶች ምንድን ናቸው?
የእስራኤል እና የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ ጦርነት ከጀመሩ አራተኛ ወራቸውን ይዘዋል
እስራኤል ጦርነቱ ወደ አዲስ ምዕራፍ መግባቱን በመግለጽ፣ የተወሰነ ኃይሏን ከጋዛ እንደምታስወጣ አስታውቃለች
በእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት የተከሰቱ አዳዲስ ሁነቶች ምንድን ናቸው?
የእስራኤል እና የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ ጦርነት ከጀመሩ አራተኛ ወራቸውን ይዘዋል።
እስራኤል ባለፈው ጥቅምት ወር ያልተጠበቀ ጥቃት አድርሶ 1200 ዜጎቿን የገደለባትን እና 240 የሚሆኑ ያገተባትን ሀማስን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት መጠነሰፊ ዘመቻ ከፍታለች።
እስራኤል ጋዛን እያስተዳዳረ ባለው ሀማስ ላይ ተከታታይ የአየር ጥቃት ካደረሰች በኋላ የእግረኛ ጦር በማዝመት የጋዛ ከተማን ተቆጣጥራለች።
የጋዛ ሰርጥ ከተሞችን የተቆጣጠረችው እስራኤል ሀማስ መሽጎባቸዋል ያለቻቸውን ቦታዎች ስታስስ ቆይታለች።
አሁን ላይ እስራኤል ጦርነቱ ወደ አዲስ ምዕራፍ መግባቱን በመግለጽ፣ የተወሰነ ኃይሏን ከጋዛ እንደምታስወጣ አስታውቃለች።
አንድ የእስራኤል ባለስልጣን እንደተናገሩት እስራኤል በሀማስ ላይ ኢላማቸውን የጠበቁ ጥቃቶች ወደመሰንዘር እንደምትገባ እና ጦርነቱ እስከአመቱ መጨረሻ ሊቆይ ስለሚችል ኢኮኖሚውን ለማገዝ ግማሹን ተጠበባቂ ኃይል ወደ መደበኛ ስራ እንደምትመልስ ተናግረዋል።
የእስራኤል ጦር ባወጣው መግለጫ አምስት ብርጌዶች ወይም በበርካታ ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ከጋዛ እንደሚወጡ ገልጿል።
እስራኤል ሀማስን ማስወገድ ቀዳሚ አጀንዳዋ ቢሆንም በሁለተኛው ግንባር ከሄዝቦላህ ጋር ለሚኖረው ግጭት ዝግጅት እንደምታደርግ ሮይተርስ ዘግቧል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኒታንያሁ በቅርቡ የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ለወራት ሊቆይ እንደሚችል መናገራቸው ይታወሳል።
በጋዛ ለሰብአዊ እርዳታ ተኩስ እንዲቆም ሲደረግ የነበረው ጫና በአሜሪካ እና እስራኤል እምቢባይነት ሳይሳካ ቀርቷል።
የቀይ ባህር ውጥረት
የእራኤል እና ሀማስ ጦርነትን ተከትሎ በቀይ ባህር ያለው ውጥረት አይሏል።
በኢራን ይደገፋል የሚባለው የየመኑ የሀውቲ አማጺ፣ ለሀማስ አጋርነት ለማሳየት በማሰብ ወደ እስራኤል ያመራሉ በሚላቸው መርከቦች ላይ ጥቃት እየሰነዘረ ይገኛል።
ግዙፍ የመርከብ ድርጅቶችም የቀይ ባህር መስመርን ለመተው መገደዳቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።
አሜሪካ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዋጋ ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ ደህንነት ለመጠበቅ በርካታ ሀገራትን ያሳተፈ ግብረ ኃይል አቋቋማ እርምጃ በመውሰድ ላይ ትገኛለች።
ኢራን ይህን የአሜሪካ እርምጃ አትቀበለውም።
እስራኤል በጋዛ ላይ እያካሄደች ባለው ጥቃት እስካሁን 22ሺ በላይ ፍልስጤማውያ መገደላቸውን የጋዛ ባለስልጤናት ተናግረዋል።