እስከ 16 ሺህ ኪ.ግ ቦምቦችንና ክሩዝ ሚሳዔሎችን ታጥቆ ያለምንም ችግር መብረር ይችላል
ሩሲያ ከዩክሬን ጋር በገጠመችው ጦርነት ከተጠቀመችባቸው የጦር አውሮፕላኖች ውስጥ “Tu-160” አንዱ እንደሆነ ይነገራል።
በጣም ግዙፍ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ የጦር አውሮፕላን በሶቪየት ህብረት ወቅት ማለትም በፈረንጆቹ 1981 ወደ አገልግሎት የገባ ሲሆን፤ በየጊዜው ማሻሻያ እየተደረገበት እስካሁን እያገለገል ይገኛል።
ሩሲያ አውሮፕላኑ ላይ በፈረንጆቹ 2008 አዳዲስ ማሻሻዎንብመ በማድረግ ይፋ ያደረገች ሲሆን፤ Tu-160R በሚል ስያሜ የአየር ኃይሏን ዳግም አስታጥቃለች።
ለመሆኑ ግዙፉ Tu-160 የጦር አውሮፕላንን ምን የተለየ ያደርገዋል?
የአወሮፕላ ቁመት 54.1 ሜትር ሲሆን፤ ክንፉ ርዝማኔም 35.6 ሜትር ይረዝማል፤ ክንፎቹ ላይ አራት ኩዜንትዞቭ NK-321 ቱርቦፋን ሞተሮች ተገጥመውለታል።
አውሮፕላኑ ከመሬት እስከ 52ሺ ገጫማ ወደላይበመነሳት መብረር ይችላል ተብሏል።
ሱፐርሶኒክ ፍጥነት እንዳለው የተነገረው Tu-160 የጦር አውሮፕላን በሰዓት 1,236 ኪሎ ሜትሮች መብረር የሚችል መሆኑም ይነገርለተል።
Tu-160 የጦር አውሮፕላን 16,330 ኪ.ግ የሚመዝኑ ቦምቦችን ተሸክሞ በሱፐርሶኒክ ፍጥነት መብረር የሚችል ነው ተብሏል።
አውሮፕላኑ ከቦምቦች በተጨማሪም Kh-101 እና Kh-102 የሚባሉ ክሩዝ ሚሳኤሎችን መታጠቅ የሚችል እና ኢላማውን በአግባ የሚመታ መሆኑም ተነግሯል።