አሜሪካዊው ወታደር ሩሲያ ውስጥ መታሰሩን ጦሩ አስታወቀ
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ሞስኮ የዋል ስትሪት ጋዜጠኛውን ኢቫን ገርሽኮቪችን ጨምሮ በርካታ አሜሪካውያንን እንድትለቅ እያግባቡ ነው
የወንጀል ድርጊት በመፈጸም የተከሰሰው የአሜሪካ ወታደር ሩሲያ ውስጥ በታሰሩን የአሜሪካ ጦር በትናንትናው እለት አስታውቋል
የወንጀል ድርጊት በመፈጸም የተከሰሰው የአሜሪካ ወታደር ሩሲያ ውስጥ በታሰሩን የአሜሪካ ጦር በትናንትናው እለት አስታውቋል።
ሮይተርስ ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገን የአሜሪካ ባለስልጣን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ወታደሩ በደቡብ ኮሪያ ተሰማርቶ የነበረ ነው።
ሌላው ባለስጣን ደግሞ ወታደሩ ከሴት በመስረቅ ክስ እንደቀረበበት ተናግረዋል።
ጉዳዩ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው በመሆኑ ጦር የክሱን ዝርዝር ማብራራት አልፈለገም ተብሏል። ጦሩ እንደገለጸው ሞስኮ ወታደሩን በወንጀል ድርጊት ከሳ ማሰሯን የቬና ስምምነት በሚያዘው መሰረት ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቃለች።
"ግንቦት 2፣2024 በሩሲያ ቭላድቮስቶክ የሚገኙ የሩሲያ ባለስልጣናት የአሜሪካ ወታደርን በወንጀል ድርጊት ከሰው አስረዋል" ብሏል የአሜሪካ ጦር።
ሮይተርስ ስለጉዳዩ በአሜሪካ፣ ዋሽንግተን ከሚገኘው የሩሲያ ኢምባሲ መልስ እንዳላገኘ ገልጿል።
ሮይተርስ የሩሲያውን እለታዊ ጋዜጣ ኢዝቨስቲያን ጠቅሶ እንደዘገበው በደቡብ ኮሪያ መቀመጫውን አድርጎ የነበረው ይህ ወታደር በሩሲያ የሩቅ ምስራቅ ወደብ ቭላድቮስቶክ ከምትኖር ሩሲያዊት ሴት ጋር በኢንተርኔት አማካኝነት ተዋውቋል።
ጥንዶቹ አበረው መኖር ከጀመሩ በኋላ ወታደሩ በጥፊ መትቶ 2200 ዶላር እንደቀማት ተገልጿል።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ሞስኮ የዋል ስትሪት ጋዜጠኛውን ኢቫን ገርሽኮቪችን ጨምሮ በርካታ አሜሪካውያንን እንድትለቅ እያግባቡ ነው።
ባለፈው አመት በፌደራል ሴኩሪቲ ሰርቪስ የታሰረው የ32 አመቱ ገርሽኮቪች፣ ከቀዝቃዛው ጦርነት ወዲህ በሰላይነት ተጠጥሮ ሩሲያ ውስጥ የታሰረ የመጀመሪያው አሜሪካ ጋዜጠኛ ሆኗል።
ጋዜጠኛው፣ የሚሰራበት ጋዜጣ እና አሜሪካ ሰላይ ነው የሚለውን ክስ አይቀበሉትም።