ፕሬዝዳንት ፑቲን ምእራባውያን በእስያ አዲስ "ኔቶ" አይነት ጥምር የጦር ለመፍጠር ይፈልጋሉ ሲሉ ከሰሱ
ፑቲን፤ የአሜሪካ አፈ ጉባዔ የታይዋን ጉብኝት የቀጠናውን ውጥረት ለማባበስ "ታቅዶ የተደረገ ትንኮሳ" ነው ብለዋል
“ሩሲያ የጦር ሀይሏን ለማጠናከር እና የጸጥታ መዋቅሯን ለማጎልበት ቆርጣ መሳቷን ፕሬዝዳንት ፑቲን አስታውቀዋል
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፤ የምዕራቡ ዓለም ሀገራት በእስያ-ፓሲፊክ ቀጠና የ"ኔቶ" አይነት ጥምር የጦር ኃይል ማደራጀት ይፈልጋሉ ሲሉ ከሰዋል።
ፕሬዝዳንቱ በሞስኮ ዓለም አቀፍ የጸጥታ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ፤ “አሜሪካ በዩክሬን ያለውን ግጭት ለማራዘም እየሞከረች ነው” ሲሉም ተደምጠዋል።
የቅርቡ የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት ውጥረቶች ለማባበስ “ታቅዶ የተደረገ ትንኮሳ” አድርገው እንደሚቆጥሩትም ተናግረዋል።
በዓለም ላይ ያለው ሁኔታ ፈጣንና ተለዋዋጭ እየሆነ በመምጣቱን በርካታ ሀገራትት ለሉዓላዊነታቸው ቅድሚያ በመስጠት በመስራት ላይመሆናቸው ፕሬዝዳንት ፑቲን አንስተዋል።
ሩሲያ ከአጋሮቿ እና ተመሳሳይ አስተሳሰብ ካላቸው ሀገራት ጋር በመሆን አሁን ያሉትን ዓለም አቀፍ ደኅንነት ስልቶችን ጨምሮ አዳዲስ ስልቶችን በመፍጠር ለማሻሻል እንደምትሰራ አስታውቀዋል።
“በወታደራዊው ዘርፍ ሩሲያ የጦር ሀይሏን ለማጠናከር እና የጸጥታ መዋቅሯን ለማጎልበት ቆርጣ ተነስታለች”ም ብለዋል ፑቲን።
በፖለቲካዊ መስክም እንዲሁ መብቶችን የሚጠብቅ ፣ የባህል እና የስልጣኔ ብዝሃነትን የሚደግፍ ዴሞክራሲያዊ ዓለም ለመገንባት የሚያግዙ እርምጃዎችን ለመውሰድ የሚቻላት ጥረት ታደርጋለች ሲሉ ተደምጠዋል።
ፕሬዝዳንተ ፑቱን በዩክሬን ስላለው ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ሲናገሩም በዩክሬን ያለው ቀውስ እንዲባባስ አሜሪካ አሉታዊና ሚና እየተጫወተች እንደምትገኝ ተናግረዋል፡፡
እንደ ሩሲያ ሁሉ በታይዋን ጉዳይ ከአሜሪካ ጋር መካረር ውስጥ የገባችው ቻይና፤ በዩክሬን ለተፈጠረው ዩክሬን ቀውስ “ዋና ቀስቃሽ” አሜሪካ ናት ስትል በቅርቡ ዋሽንግተንን መክሰሷ አይዘነጋም።
በሞስኮ የቻይና አምባሳደር ዣንግ ሃንሁዊ ረቡዕ ታትሞ ከወጣው የሩስያ መንግስት የዜና ወኪል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ፤ ዋሽንግተን በኔቶ የመከላከያ ህብረት ተደጋጋሚ መስፋፋት በማድረግና እና ዩክሬንን ከአውሮፓ ህብረት ጋር ለማስማማት ለሚፈልጉ ሃይሎች ድጋፍ በመስጠት ሩሲያን ወደ ጥግ እየገፋቸው ነው በማለት ከሰዋል።