የአሜሪካ እርዳታ ዩክሬን የበለጠ እንድትፈራርስ የሚያደርግ ነው-ክሬሚሊን
ዘለንስኪ የጸደቀው እርዳታ ጦርነቱ እንዳይስፋፋ የሚያደርግ እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከሞት የሚታደግ ነው ብለዋል
አሜሪካ ተወካዮች ምክር ቤት ለዩክሬን ወታደራዊ እርዳታ ለመስጠት ያሳለፈው ውሳኔ አሜሪካን የሚያበለጽግ እና ዩክሬንን የለበጠ ድሃ የሚያደረግ ነው ሲሉ የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ድሜትሪ ፔስኮቭ አጣጥለውታል
የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለዩክሬን ወታደራዊ እርዳታ ለመስጠት ያሳለፈው ውሳኔ አሜሪካን የሚያበለጽግ እና ዩክሬንን የለበጠ ድሃ የሚያደረግ ነው ሲሉ የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ድሜትሪ ፔስኮቭ አጣጥለውታል።
ፔስኮቭ "ለዩክሬን ወታራዊ ድጋፍ ለመስጠት የተላለፈው ውሳኔ የሚጠበቅ እና የሚተነበይ ነበር። ይህ አሜሪካን የበለጠ የሚያበለጽግ እና ዩክሬንን የበለጠ የሚያፈራርስ እንዲሁም ብዙ ዩክሬናውያን እንዲገደሉ የሚያደርግ ነው" ማለታቸውን ሲጂቲኤን የሩሲያውን ታስ ዜና አገልግሎት ጠቅሶ ዘግቧል።
የአሜሪካው የተወካዮች ምክርቤት ለዩክሬን፣ ለእስራኤል እና በኢንዶ ፓሲፊክ ለሚገኙ የአሜሪካ አጋሮች የሚወል የ95 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ በትናንትናው እለት አጽድቋል።
የምክር ቤቱ ውሳኔ እንዳይንቀሳቀስ የተደረገው የሩሲያ ሀብት ተወርሶ ዩክሬንን ለመደጎም የሚያስችሉ እርምጃዎችን ማካተቱም ተገልጿል።
"የእኛን ሀብት ስለመውረስ የምናወራ ከሆነ፣ ይህ የአሜሪካን ስም የሚያበላሽ ነው። የግለሰብ ሀብት የማፍራት መብት የሚጣስ ከሆነ በሀገሪቱ ያሉ ብዙ ኢንቨስተሮች ይሸሻሉ" ብለዋል ፔስኮቭ።
የዩክሬን ድጋፍ 311-112 ድምጽ በምክር ቤቱ ሊጸድቅ ችሏል። በዲሞክራቱ ፕሬዝደንት ባይደን አስተዳደር የቀረበውን የድጋፍ እቅድ 112 የሪፐብሊካን አባላት የደገፉት ሲሆን 101 ደግሞ ተቃውመውታል።
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ እርዳታው በምክር ቤቱ መጽደቁን ተከትሎ የአሜሪካ የተወካዮች ምክርቤት አባላት "ታሪክን በትክክለኛው መንገድ አስቀጥለዋል" ሲሉ አመስግነዋል።
ዘለንስኪ የጸደቀው እርዳታ ጦርነቱ እንዳይስፋፋ የሚያደርግ እና በሺዎቸ የሚቆጠሩ ሰዎች ከሞት የሚታደግ ነው ብለዋል።