ዩክሬን የሩሲያን ጥቃት መከላከያ "ሚሳይል አልቆብኛል" አለች
ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ቀደም ሲል የሩሲያ ሚሳይል ጥቃት የማይቀንስ ከሆነ ዩክሬን የመከለከያ ሚሳይሎች ሊያልቅባት እንደሚችል አስጠንቅቀው ነበር
ሩሲያ በኪቭ አቅራቢያ ያለውን 1800 ሜጋ ዋት ኃይል የሚያመነጨውን ግዙፉን የትራይፒሊስካን የተርማል ኃይል ጣቢያን አውድማለች
ዩክሬን የሩሲያን ጥቃት መከላከያ "ሚሳይል አልቆብኛል" አለች።
በአየር መካለከያ ሚሳይል እጥረት ምክንያት ባለፈው ሳምንት በኪቭ አቅራቢያ በሚገኘው የኃይል ጣቢያ ላይ የተወነጨፈውን ሩሲያ ሚሳይል ማክሸፍ ሳይቻል መቅረቱን ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ተናግረዋል።
ዘለንስኪ ለአጋሮቻቸው ተደጋጋሚ የእርዳታ ጥሪ ማድረጋቸውን ተከትሎ የሰጡት ይህ አስተያየት ዩክሬን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መሆኗን የሚያመላክት ነው ተብሏል።
"11 ሚሳይሎች ተወነጨፉ። ሰባቱን ስናከሽፍ አራቱ ቀሩ። ለምን?፤ ምክንያቱም ሚሳይል አለቀብን። ትራይፒላን ለመከላከል የሚሆን ሚሳይል አለቀብን" ሲሉ ዘለንስኪ ፒቢኤሰ ከተባለ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ መናገራቸውን ሮይተረስ ዘግቧል።
ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ቀደም ሲል የሩሲያ ሚሳይል ጥቃት የማይቀንስ ከሆነ ዩክሬን የመከለከያ ሚሳይሎች ሊያልቅባት እንደሚችል አስጠንቅቀው ነበር
የዩክሬንን የኃይል መሰረተ ልማቶች ኢላማ ያደረገቸው ሩሲያ በኪቭ አቅራቢያ ያለውን 1800 ሜጋ ዋት ኃይል የሚያመነጨውን ግዙፉን የትራይፒሊስካን የተርማል ኃይል ጣቢያን ጨምሮ በርካታ የኃይል ጣቢያዎችን አውድማለች።
ሩሲያ ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ ድሮን እና ሚሳይል በመጠቀም በዩክሬን የኃይል መሰረተ ልማት ላይ የምታርገውን ጥቃት አጠናክራ ቀጥላለች።
ይህ በኃይል መሰረት ልማት ላይ የደረሰው ጥቃት ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ዘመቻ ከከፈተችበት ወዲህ ሁለተኛው ከባድ ጥቃት ነው ተብሏል።
ባለፉት ሳምንታት ዩክሬን ሰባት ጊጋዋት ኃይል የማመንጨት አቅሟን አጥታለች።
ዩክሬን ግዛቷን በሚገባ ከጥቃት ለመከላከል 25 አሜሪካ ሰራሽ ፓትሪዎት ሚሳይል እንደምትፈልግ ብትገልጽም፣ ምዕራባውያን አጋሮቿ ተጨማሪ አየር መከላከያ ሚሳይል አላኩላትም።
የሩሲያ- ዩክሬን ጦርነት ሁለት አመት ያለፈው ሲሆን ሩሲያ በምስራቅ ዩክሬን ያሉ አራት ግዛቶችን ሙሉ በሙሉ ለመጠቅለል አየተዋጋች ትገኛለች።