ኬቭ ከአሜሪካ እና አጋሮቿ ተጨማሪ ወታደራዊ ድጋፍ እንዲደረግላት እየጠየቀች ነው
አሜሪካ በየአመቱ ለሀገራት በቢሊየን ዶላር የሚገመት ድጋፍ ታደርጋለች።
የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ወደ ኬቭ የላከችው ድጋፍ ግን እጅግ ከፍተኛ መሆኑን የጀርመኑ የጥናት ተቋም ኬል ኢንስቲትዩት ያወጣው መረጃ ያሳያል።
ከየካቲት 2022 እስከ የካቲት 2023 ብቻ ከ76 ቢሊየን ዶላር በላይ የሰብአዊ እና ወታደራዊ ድጋፍ ማድረጓን ተቋሙ ገልጿል።
ይህም አሜሪካ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ “ማርሻል እቅድ” በሚል የአውሮፓ ሀገራትን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት ካደረገችው ድጋፍ የሚልቅ መሆኑንም በመጥቀስ።
የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) እና የአውሮፓ ሀገራትም ለኬቭ ወታደራዊ ድጋፋቸውን ቀጥለዋል።
ይሁን እንጂ በአለማችን ጠንካራ ሰራዊት የገነባችውን ሩሲያ ጥቃት ለመመከት አሁንም ተጨማሪ ወታደራዊ ድጋፍ ያስፈልገኛል እያለች ነው።
አሜሪካ 16ኛ ወሩን በያዘው ጦርነት ለዩክሬን ምን ያህል ድጋፍ አደረገች? ዝርዝሩን ይመልከቱ፦