የአሜሪካ አየር ኃይል በትራምፕ መኖሪያ ቤት አቅራቢያ ሲበሩ የነበሩ ሁለት ሄሊኮፕተሮችን እንዲመለሱ ማድረጉን አስታወቀ
የፌደራል ባለስልጣናት ትራምፕ በመኖራያቸው በሚሆኑበት ወቅት ከትራምፕ ክለብ 30 ማይል ሪዲየስ ውስጥ ቋሚ የሆነ የበረራ ክልከላ አድርገዋል

ሄሊክፕተሮቹ ወደተከለከለው ቦታ የበረሩት ፕሬዝደንት ትራምፕ በዌስት ፓልም ቢች በሚገኘው የጎልፍ ሜዳቸው አንድ ዙር ጨዋታ ከጨረሱ በኋላ ነው ተብሏል
የአሪካ አየር ኃይል ጄቶች በትናንትናው እለት በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፊሎሪዳ መኖሪያ ቤት አቅራቢያ በጊዜያዊነት በተከለከለ ቦታ ሲበሩ የነበሩ ሁለት የሲቪሊያን ሄሊኮፕተሮች እንዲመለሱ ማድረጉን የሰሜን አሜሪካ ኤየሮስፔስ ዲፌንስ ኃይል እዝ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ይህ ጥሰት ፕሬዝደንት ትራምፕ ባለፈው ጥር ወር ወኃይትሀውስ ከገቡ በኋላ የተፈጸሙ ጥሰቶችን ወደ 20 ከፍ እንዲሉ ማድረጉን እዙ ጠቅሷል።
ሄሊክፕተሮቹ ወደተከለከለው ቦታ የበረሩት ፕሬዝደንት ትራምፕ በዌስት ፓልም ቢች በሚገኘው የጎልፍ ሜዳቸው አንድ ዙር ጨዋታ ከጨረሱ በኋላ ሲሆን በኤፍ-16 ጄቶች እንዲመሱ ተደርገዋል።
በተመሳሳይ ባለፈው ቅዳሜ የአየር ኃይል ጄቶች ትራምፕ ማራ-ላ-ጎ ከተባለው ሪዞርታቸውና ከመኖሪያ ቤታቸው ወደ ጎልፍ መጫወቻ ሜዳ ካረፉ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ሲበሩ የነበሩ ሄሊኮፕተሮችን መልሰዋል።
ከፍተኛ የአየር ትራፊክ መጨናነቅ ባለበት ደቡብ ፍሎሪዳ ያሉ የአየር ክልል ጥስቶች ተዋጊ ጄቶች ክልከላ እንዲያደርጉ ቢያስገድዷቸውም፣ የትራምፕን መርሃግብር አላማስቀየራቸውን ወይም በደህንነታቸው ላይም ተጽዕኖ አለመፍጠራቸው ባለስልጣናት ተናግረዋል። ዕዙ እንዳለው ከመሬት እሳት ይታይ የነበረ ቢሆም ወዲያውኑ መጥፋቱንና ጉዳት አለመድረሱን ገልጿል።
የፌደራል ባለስልጣናት ትራምፕ በመኖራያቸው በሚሆኑበት ወቅት ከትራምፕ ክለብ 30 ማይል ሪዲየስ ውስጥ ቋሚ የሆነ የበረራ ክልከላ አድርገዋል። የአየር ክልል ጥሰቶችና ጠለፋዎች የተለመዱ ቢሆንም የክልከላ መመሪያዎችን በማይከተሉ የሲቪል አብራሪዎች ምክንያት ፕሬዝደንት ትራምፕ ስልጣን ከያዙ ወዲህ ያለው የጥስት ድግግሞች እየጨመረ ነው ሲል እዙ ሪፖርት አድርጓል።
የእዙና የአሜሪካ ሰሜን እዝ አዛዥ ጀነራል ግሪጎሪ ጉይሎት "የአየር ትራፊክ ቁጥጥር መመሪያዎችን ማክበር ለበረራ ደህንነት፣ ለብሔራዊ ደህንነት እንዲሁም ለፕሬዝደንቱ ደህንነት አስፈላጊ ነው" ብለዋል።