አሜሪካ የአልቃይዳ መሪ ነው በሚል ገድየዋለሁ ያለችው ሰው ድሃ ገበሬ ሆኖ ተገኘ
የአሜሪካ አየር ሀይል በሶሪያ ቁልፍ የአልቃይዳ መሪ ነው በሚል የተገደለው ሰው በመጨረሻም ዶሮ አርቢ ሆኖ መገኘቱን አረጋግጫለሁ ብላለች
የአልቃይዳ መሪ ነው በሚል በስህተት በአሜሪካ ጦር የተገደለው ሰው የ60 ዓመት ሶሪያዊ አርሶ አደር ነበር
አሜሪካ የአልቃይዳ መሪ ነው በሚል ገድየዋለሁ ያለችው ድሃ ገበሬ ሆኖ ተገኘ፡፡
የአሜሪካ አየር ሀይል ጦር በሶሪያ የሚንቀሳቀሰው አልቃይዳ ቁልፍ አመራር ነው በሚል ነበር የድሮን ጥቃት የፈጸመው፡፡
ጥቃቱም ውጤታማ እንደነበር እና የአልቃይዳ አመራር መገደሉንም ሀገሪቱ አስታውቆም ነበር፡፡
ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ እንደተፈጸመ የተገለጸው ይህ ጥቃት ኢላማውን እንደሳተ እና በዶሮ እርባታ የሚተዳደር አርሶ አደር ስለመገደሉ በወቅቱ የሟች ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡
ይህ ጥቆማ የደረሰው የአሜሪካ አማዕከላዊ እዝም ባደረገው ማጣራት በወቅቱ በተፈጸመው ጥቃት የተባለው የአልቃይዳ መሪ ሳይሆን ሉፍቲ ሀሰን ማስቶ የተሰኘ ዶሮ አርቢ አርሶ አደር እንደተገደለ ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡
የአሜሪካ ማዕከላዊ እዝ ይፋ ባደረገው ምርመራ የ60 ዓመቱ አዛውንት በተፈጸመው የድሮን ጥቃት እንደተገደለ ይህም ስህተት መሆኑን አረጋግጠናልም ብሏል፡፡
በአሜሪካ የሰው አልባ አውሮፕላን ወይም ድሮን ጥቃት በስህተት የተገደለው ማስቶ ወንድም በበኩሉ ወንድሙ ዶሮ ከማርባት እና በግ ከመንዳት ውጪ ከአልቃይዳም ሆነ ከየትኛውም ቡድን ጋር ግንኙነት የሌለው ሰው ነው ብሏል፡፡
የሩሲያ ወታደሮች የአሜሪካ ጦር ወደሚኖርበት የጦር ሰፈር ገቡ
በወምድሜ ላይ ግፍ ተፈጽሟል የሚለው ይህ የሟች ወንድም ጥቃቱ የተፈጸመበት በግ እየነዳ ባለበት ወቅት ነው ሲልም አክሏል፡፡
እንደ ኤንቢሲ ዘገባ የአሜሪካ ማዕከላዊ እዝ ቁልፍ የአልቃይዳ የሽብር ቡድን አመራር ነው በሚል የፈጸመው ጥቃት በስህተት ንጹህ ሰው መግደሉን ያረጋገጠው ባሳለፍነው ህዳር ወር ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡
እዙ የምርመራ ሪፖርቱን ለምን እንዳዘገየው እስካሁን ያልተናገረ ሲሆን በቀጣይ ተመሳሳይ ስህተት እንዳይፈጸም የማሻሻያ እርምጃዎችን መውሰድ አለብን ማለቱንም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
የአሜሪካ ጦር በአፍጋኒስታን፣ ኢራን እና ሶሪያ በሚፈጽማቸው የአየር ላይ ጥቃቶች በተለያዩ ጊዜያት ንጹሃንን ኢላማ አድርጓል የሚሉ ሪፖርቶች ሲቀርቡበት ቆይቷል፡፡