“ትሸታላችሁ” በሚል ጥቁር መንገደኞችን ከበረራ ላይ ያስወረዱ ሰራተኞች ከስራ ተባረሩ
ከበረራ ላይ እንዲወርዱ የተደረጉት ጥቁር መንገደኞች በአየር መንገዱ ላይ ክስ መስርተው ነበር
መንገደኞቹ ከአሪዞና ወደ ኒዮርክ ለመብረር ወንበራቸው ላይ እያሉ ነበር በበረራ አስተናጋጅ አማካኝነት እንዲወርዱ የተደረጉት
“ትሸታላችሁ” በሚል ጥቁር መንገደኞችን ከበረራ ላይ ያስወረዱ ሰራተኞች ከስራ ተባረሩ፡፡
ከፎኒክስ አሪዞና ወደ ኒዮርክ ለመጓዝ ወንበራቸው ላይ የነበሩ ጥቁር አሜሪካዊያን በበረራ አስተናጋጅ አማካኝነት ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ይነገራቸዋል፡፡
ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ በተፈጠረው በዚህ ክስተት የበረራ አስተናጋጁ ጥቁር አሜሪካዊያንን መርጦ ለምን እንዳስወረዳቸው ሲጠየቅም ከተሳፋሪዎቹ ውስጥ መጥፎ ሽታ ያለው መንገደኛ በመኖሩ ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል ተብሏል፡፡
በተለያዩ ወንበሮች ላይ የተቀመጡት እና የማይተዋወቁት እነዚህ አምስት ጥቁር አሜሪካዊያን መጥፎ የሰውነት ሽታ አለ በሚል ከየተቀመጥንበት ተመርጠን እንድንወርድ መደረጋችን ግልጽ ዘረኝነት ነው ሲሉ በጋራ ባወጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም በረራው ቢዘገይም በዚሁ አውሮፕላን አብረው እንዲጓዙ ከተደረጉ አምስት ጥቁር አሜሪካዊያን መካከል ሶስቱ ክስ መስርተውም ነበር፡፡
የቻይና ምርት የሆነው “C919” የመንገደኞች አውሮፕላን ለመብረር የሚያስችለውን ፈቃድ አገኘ
ለደረሰብን የዘረኝነት ጥቃት አየር መንገዱ ካሳ ሊከፍለን ይገባል ሲሉ ክስ የመሰረቱት እነዚህ ሶስት አሜሪካዊያን በተፈጠረው ክስተት ማዘናቸውን ተናግረዋል፡፡
ክስ የቀረበበት የአሜሪካን አየር መንገድ በወቅቱ ጉዳዩን እየመረመረ መሆኑን ገልጾ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ በወቅቱ በስራ ላይ የነበሩትን ሁሉ ከስራ ማባረሩን አስታውቋል፡፡
ጉዳዩ በፍጹም ተቀባይነት የለውም ያለው አየር መንገዱ መንገደኞችን ማበላለጥ ፍጹም ከሙያ ስነ ምግባር በመሆኑ እርምጃ እንደወሰደባቸው ገልጿል፡፡
በፈረንጆቹ 2017 ላይ አንድ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ጥቁር አሜሪካዊያን ዘረኝነት እና መድሎዎችን ለመራቅ በአሜሪካን አየር መንገዶች እንዳይበሩ ሲል አስጠንቅቆ የነበረ ሲሆን አየር መንገዶች ማስተካከያ አድርገናል ማለታቸውን ተከትሎ ማስጠንቀቂያውን አንስቷል፡፡