የአሜሪካ አየር መንገዶች በኦሚክሮን ምክንያት ወደ 1ሺ የሚጠጉ የገና ቀን በረራዎችን ሰረዙ
በስረዛው ብዙ ከተጠቁት 10 የአለም አየር ማረፊያዎች ስድስቱ የቻይና ናቸው ተብሏል
በረራዎች ከመሰረዛቸው በተጨማሪ ወደ 2,000 የሚጠጉ በረራዎች እንዲዘገዩ መገደዳቸው ተገልጿል
በአሜሪካ አየር መንገዶች ቅዳሜና እሁድ ሊደረጉ የነበሩ ወደ 1,000 የሚጠጉ በረራዎች መሰረዛቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የኮሮና ቫይረስ እጨመረ መምጣቱ እና በኮሮና ተይዘው ራሳቸውን የሚያገሉ ፓይለቶችና የክሪው አባላት በመኖራች ምክንያት እቅዳሜ እና እሁድ ሊደረጉ በነበሩ በረራዎች ሊጓዙ የነበሩ በአስርሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን እቅድ አስተጓጉሏል፡፡
ፍላይት አዌር የተባለው የበረራ መከታተያ ድረ-ገጽ እንዳመለከተው በአጠቃላይ 957 የገና ቀን በረራዎች፣ የሀገር ውስጥ በረራዎችን እና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ወይም የሚወጡትን ጨምሮ፣ በገና ዋዜማ ከ690 በላይ በረራዎች ተሰርዘዋል፡፡
በረራዎች ከመሰረዛቸው በተጨማሪ ወደ 2,000 የሚጠጉ በረራዎች መዘግየታቸው ተገልጿል፡፡
ቢያንስ አንድ አየር መንገድ በዛሬው እለት በመቶዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ስረዛዎችን እንደሚጠብቅ ተናግሯል።
ሮይተርስ እንደዘገበውየገና በዓላት በተለምዶ ለአየር ጉዞ ከፍተኛ ጊዜ ናቸው፤ ነገር ግን በጣም የሚተላለፈው የኦሚክሮን የኮሮና አይነት በፍጥነት መስፋፋቱ በከፍተኛ ቁጥር ሰዎች እየተጠቁ ነው፤ ይህም አብራሪዎች እና የበረራ ሰራተኞች ራሳቸውን ማግለል ስላለባቸው አየር መንገዶች በረራዎችን እንዲሰርዙ አድጓቸዋል፡፡
ዩናይትድ አየር መንገድ (UAL.O) ብቻ 230 በረራዎችን የሰረዘ ሲሆን የአሜሪካ አየር መንገድ ደግሞ 90 በረራዎችን ማቋረጡን የኩባንያዎቹ ተወካዮች በተለያዩ መግለጫዎች ሰጥተዋል።
ዩናይትድ አየር መንገድ ቃል አቀባይ ማዲ ኪንግ “በዚህ ሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ በኦሚክሮን ጉዳዮች ላይ ያለው ጭማሪ በበረራ ሰራተኞቻችን እና ስራችንን በሚመሩ ሰዎች ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል” ብለዋል ።
በአለም አቀፍ ደረጃ የፍላይት አዌር መረጃ እንደሚያሳየው ቅዳሜ ከ 2,700 በላይ በረራዎች ተሰርዘዋል፤ ሌሎች 7,049 በራዎች ዘግይተዋል፡፡
ከፍተኛ ተጽዕኖ ከደረሰባቸው የዩኤስ አየር ማረፊያዎች መካከል የአትላንታ ሃርትስፊልድ-ጃክሰን ኢንተርናሽናል፣ የኒውጀርሲው ኒውርክ ሊበርቲ ኢንተርናሽናል፣ ሎስ አንጀለስ ኢንተርናሽናል እና የኒውዮርክ ጄኤፍኬ ኢንተርናሽናል ይገኙበታል።
በመሰረዙ ብዙ ከተጠቁት 10 የአለም አየር ማረፊያዎች ስድስቱ የቻይና ናቸው ተብሏል፡፡
ባለፈው ሳምንት በየቀኑ አማካይ የአሜሪካ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር በ45% ወደ 179,000 ከፍ ማለቱን ሮይተርስ ዘግቧል።