አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአጎአ ተጠቃሚነት የሰረዘችው ከሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ መሆኑን አስታውቃለች
የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ባስተላለፉት ውሳኔ ኢትዮጵያ ከቀረጥና ከኮታ ነጻ ከሆነው የንግድ ችሮታ (አጎአ) ተጠቃሚነት ሙሉ ለሙሉ ተሰርዛለች፡፡
አሜሪካ፣ተፈጽመዋል በተባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ምክንያት ኢትዮጵያ የንግድ ችሮታው ተጠቃሚ ለመሆን ቅድመ ሁኔታዎችን እንደማታሟላ ባለፈው ህዳር ወር ለኢትዮጵያ መንግስት ማሳወቋን ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡
- ኢትዮጵያ ከአሜሪካው አጎአ እንድትወጣ “የሚጎተጉቱ”ት እነማን ናቸው?
- አሜሪካ አጎአን አስመልክቶ ያሳለፈችውን ውሳኔ እንድትሰርዝ ኢትዮጵያ ጠየቀች
- ጆ ባይደን ኢትዮጵያን ከአሜሪካ ንግድ ችሮታ (አጎአ) ማስወጣታቸውን ለኮንግረሱ አሳወቁ
በአሜሪካ መንግስት ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ ሀገራት የሚሰጠው ከቀረጥና ከኮታ ነጻ የሆነው የንግድ ችሮታ (አጎአ) በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቢል ክሊንተን ዘመን የተፈረመ ነው። ይህ የንግድ ችሮታ 20 ዓመት አልፎታል።
ኢትዮጵያ ከዚህ የገበያ እድል የተሰረዘችው በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ጦርነት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ መብት ተጥሷል በሚል እና ይሄንን እንድታስተካከል የሁለት ወራት ጊዜ ተሰጥቷት ባለማስተካከሏመሆኑን የፕሬዘዳንቱ ውሳኔን ዋቢ አድርጎ ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡
ከኢትዮጵያ በተጨማሪም ምዕራብ አፍሪካዊያኑ ማሊ እና ጊኒም ከአግዋ እድል በአሜሪካ የተሰረዙ ሀገራት ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት የአግዋ እድል በሰሜን ኢትዮጵያ ካለው ጦርነት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም ውሳኔው በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ ከእድሉ ተጠቃሚ የነበሩ ከ1 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ህይወት ይጎዳል ስትል ቆይታለች፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት፣ አሜሪካ ውሳኔዋን እንድትቀለብስ በተደጋጋሚ ጠይቆ ነበር፡፡