በኢራቅ እና በሶሪያ ባለው የአሜሪካ ጦር ላይ ለደሰረው ጥቃት ኃላፊነቱን የወሰደው ማነው?
ባለስሌጣናቱ እንደገለጹት ከባለፈው ሀሙስ ጀምሮ በኢራቅ 36፣ በሶሪያ ደግሞ 37 ጥቃቶች ተፈጽመዋል
ራሱን የእስላሚክ ሪዚስታንስ ብሎ የሚጠራው ቡድን በእነዚህ ቦታዎች ለደረሰው ጥቃት ኃላፊኑን ወስዷል
በኢራቅ እና በሶሪያ ያለው የአሜሪካ ጦር አራት ጊዜ ጥቃት ደረሰበት
በኢራቅ እና በሶሪያ የሚገኘው የአሜሪካ ጦር በድሮን እና በሮኬት አራት ጊዜ ጥቃት እንደደረሰበት የአሜሪካ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
በጥቃቱ በሰውም ይሁን በመሰረተ ልማት ላይ ጉዳት አለመድረሱን ሮይተረስ ዘግቧል።
ባለስልጣቱ እንደገለጹት በሰሜን ምስራቅ ሶሪያ የሚገኘው የአሜሪካ ጦር በበርካታ ሮኬቶች እና በድሮን ጥቃት ደርሶበታል። በኢራቅ አይን አል አል አሳድ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ በአንድ ጊዜ በበርካታ ድሮኖች ጥቃት ተፈጽሞበታል ተብሏል።
ራሱን የእስላሚክ ሪዚስታንስ ብሎ የሚጠራው ቡድን በእነዚህ ቦታዎች ለደረሰው ጥቃት ኃላፊኑን ወስዷል።
በአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት የተሰነዘረው አሜሪካ በኢራን በሚደገፈው ካታይብ ሄዝቦላ ላይ ጥቃት ካደረሰች ከአንድ ቀን በኋላ ነው።
ይህን ጥቃት የኢራቅ መንግስት ሉአላዊነትን የሚጥስ ነው በሚል አውግዞታል።
የአሜሪካ ባለስሌጣናት የእሴራኤል እና ሀማስ ጦርነት ከተጀመረ ከ10 ቀናት በኋላ በአሜሪካ እና ሌሎች አለምአቀፍ ኃይሎች ላይ ትንኮሳዎች በመፈጸማቸው ምክንያት ጥቃት ማድረሷን ተናግረዋል።
ባለስሌጣናቱ እንደገለጹት ከባለፈው ሀሙስ ጀምሮ በኢራቅ 36፣ በሶሪያ ደግሞ 37 ጥቃቶች ተፈጽመዋል።