አሜሪካ ስልጣን የያዙ የኒጀር ወታደሮችን ለማስገደል እያሴረች መሆኗ ተገለጸ
ግድያው በአሜሪካ ወታደራዊ ተቋማት ስልጠና በወሰዱ የኒጀር ወታደሮች ሊፈጸም ይችላል ተብሏል
በኒጀር በተፈጸመ መፈንቅለ መንግስት ጀነራል ቲያኒ የሀገሪቱ መሪ ነኝ ማለታቸው ይታወሳል
አሜሪካ ስልጣን የያዙ የኒጀር ወታደሮችን ለማስገደል እያሴረች መሆኗ ተገለጸ፡፡
ፈረንሳይን ጨምሮ የምዕራባዊያን ሀገራት ቁልፍ አጋር በመባል በምትታወቀው ኒጀር ከአንድ ወር በፊት በተፈጸመ መፈንቅለ መንግስት የሀገሪቱ ጦር ስልጣን መቆጣጠሩ ይታወሳል፡፡
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጥበቃ ክፍል ዋና አዛዥ የሆነችው ጀነራል አብዱሮህማን ቲያኒ የወቅቱ የኒጀር መሪ መሆናቸውን ካወጁ በኋላ በርካታ ማዕቀቦች እና የዛቻ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው፡፡
የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ወይም ኢኮዋስ ስልጣን በሀይል የተቆጣጠረው የኒጀር ወታደራዊ ቡድን ለቀድሞው ፕሬዝዳንት ባዙም ስልጣን ካላስረከበ ወታደራዊ እርምጃ እወስዳለሁ ማለቱ ዋነኛው ነው፡፡
በኒጀር ወታደሮቻቸውን ያሰፈሩት ፈረንሳይ አሜሪካ በበኩላቸው በኢኮዋስ የሚወሰደውን እርምጃ እንደሚደግፉ አስታውቀወም ነበር፡፡
ከዚህ በፊት መፈንቅለ መንግስት በመፈጸም ስልጣን የተቆጣጠሩት የኒጀር ጎረቤት ሀገራት በበኩላቸው ለኒጀር ወታደራዊ ቡድን ድጋፍ እንደሚያደርጉ መግለጻቸው እና ኒጀራዊያን ለጀነራል ቲያኒ ድጋፍ መስጠታቸው ኢኮዋስ ላሰበው እቅድ እንቅፋት መሆኑ ይነሳል፡፡
ስልጣን የተቆጣጠረው የኒጀር ወታደራዊ ቡድን የሩሲያው ዋግነር ቡድን እንዲረዳው ጠየቀ
ይ በዚህ እንዳለ ግን አሜሪካ ስልጣን በተቆጣጠሩት የኒጀር ወታደራዊ ቡድን ላይ ጥቃት ለመክፈት እያሴረች መሆኗን ሩሲያ ገልጻለች፡፡
ታስ የሩሲያ ስለላ ተቋምን ዋቢ በማድረግ በሰራው ዘገባ አሜሪካ የኒጀር ወታደራዊ ቡድን አመራሮች ለማስገደል እቅድ መንደፏን ገልጿል፡፡
በአሜሪካ ወታደራዊ ተቋማት ውስጥ ስልጠና የወሰዱ የኒጀር ወታደሮች ደግሞ የዋሸንግተንን የግድያ እቅድ ለማስፈጸም መመረታቸውን በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
አሜሪካ በሩሲያ በቀረበባት ክስ ዙሪያ እስካሁን ምላሽ ያልሰጠች ሲሆን ኒጀር በሀገሯ ያሉ የውጭ ሀገራት ወታደሮች ኒያሚን ለእንዲለቁ ጊዜ ገደብ አስቀምጣለች፡፡