አሜሪካ ቻይናን በዋና ጠላትነት የፈረጀች ሲሆን ቤጂንግ ዓለምን መቆጣጠር ትፈልጋለች ስትል ከሳለች
አሜሪካ ዜጎቿ በቻይና ኢንቨስት እንዳያደርጉ ከለከለች።
የአለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር አሜሪካ ቻይናን በጠላትነት የፈረጀች ሲሆን ቻይናም አሜሪካንን በተመሳሳይ ፍርጃ ውስጥ ከታታለች።
ዓለማችንን እየመራች ያለችው አሜሪካ ይህን የበላይነቷን ለመቆጣጠር እየሰራች እንደሆነም በቤጂንግ ላይ ክስ ይቀርብባታል።
በተለይም ቻይና በቴክኖሎጂ ዘርፎች የአሜሪካንን ኩባንያዎች ለራሷ ፍላጎት እየተጠቀመች ነው በሚል ከአሜሪካ ማዕቀብ ተጥሎባታል።
አሁን ደግሞ አሜሪካዊያን በቻይና ኢንቨስትመንት እንዳይሳተፉ እገዳ ማስተላለፏን ወልስትሪት ጆርናል አስነብቧል።
ዋሽንግተን ከወራት በፊት የቻይና ኩባንያዎች እና መንግሥት ከአሜሪካ ኩባንያዎች የኤሌክትሮ መካኒካል ምርቶች ወይም ችፕስ እንዳይገዙ ማዕቀብ ጥላ ነበር።
ማዕቀቡን ተከትሎም የአሜሪካ ኩባንያዎች ከቻይናን ግዙፍ የገበያ እድሎችን ለመጠቀም በሚል ወደ ቤጂንግ የመጓዝ እና ኢንዱስትሪ የማቋቋም ፍላጎት አሳይተው ነበር ተብሏል።
ይሁንና አሜሪካዊያን ባለሀብቶች እና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በቻይና ኢንቨስትመንት በከፊል አልያም ሙሉ ለሙሉ እንዳይሳተፉ ማገዷ ተገልጿል።
የእገዳው አላማም የቻይናን ዓለም የመቆጣጠር ግስጋሴን ለመግታት እንደሆነ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
አሜሪካ ቻይናን ወታደራዊ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ለሩሲያ እና ለሌሎች ሀገራት ትረዳለች በሚል የከሰሰች ሲሆን እርምጃ እንደምትወስድም አስጠንቅቃለች።