ለልጅ ማሳደጊያ 15ሺ ዶላር እንዲከፍል የተወሰነበት ናይጄሪያዊ ዶክተር ራሱን አጠፋ
መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው ናይጀሪያዊው የልብ ሀኪም ፍርድ ቤት ለልጅ ማሳደጊያ የሚሆን 15ሺ ዶላር እንዲከፍል ከወሰነበት በኋላ በብስጭት ራሱን ማጥፋቱ ተገልጿል
የዶክተር ኢሬኒ ሞት በአሜሪካ ያሉ የናይጄሪያ ማህበረሰብ አባለትን አስደንግጧል
ለልጅ ማሳደጊያ 15ሺ ዶላር እንዲከፍል የተወሰነበት ናይጄሪያዊ ዶክተር ራሱን አጠፋ።
መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው ናይጀሪያዊው የልብ ሀኪም ፍርድ ቤት ለልጅ ማሳደጊያ የሚሆን 15ሺ ዶላር እንዲከፍል ከወሰነበት በኋላ በብስጭት ራሱን ማጥፋቱ ተገልጿል።
ክስተቱ የተፈጠረው ህጻን በመያዝ እና በፋይናንስ ግዴታ ጉዳይ ከቀድሞ ባለቤቱ ጋር ረጅሙና አከራካሪው የፍርድ ሂደት በትናንትናው እለት ከተዘጋ በኋላ ነው።
በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ምክንያት የ36 አመቱ ዶክተር ኢከና ኢረኔ ከፍተኛ የገንዘብ ጫና ውስጥ ገብቷል።
በውሳኔው መሰረት ኢሬኒ የህክምና ፍቃዱ ተነጥቆ ስራ እንዲያቆምና ልጆቹን እንዳያይ ጥብቅ ክልከላ ተጥሎበታል።
ክላይቶን ኦዶ የተባለው ናይጀሪያ-አሜሪካዊ በኤክስ ገጹ ይህ ጉዳይ ወንዶች በአሜሪካ ስርዓት ውስጥ እየተሰቃዩ እንዳሉ የሚያሳይ ነው ብሏል።
ኦዶ እንዳለው "ይህ አሳዛኝ ጉዳይ ወንዶች በአሜሪካ የፍትህ ስርአት ውስጥ ተመጣጣኝ ባልሆነ መልኩ እየተጎዱ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ፍርድ ቤቱ የገንዘብና የስነልቦና አቅሙን በመጉዳት ይህ አሳዛኝ ሞት እንዲከሰት አድርጓል።"
የዶክተር ኢሬኒ ሞት በአሜሪካ ያሉ የናይጄሪያ ማህበረሰብ አባለትን አስደንግጧል።
ኦቢም ኦኑኦጂኦጉ የተባለ ሌላኛው የናይጄሪያ ማህበረሰብ አባል "ሰራና ቤተሰብ ወዳድ የሆነውን ዶክተር ኢሬኒን አጥተነዋል" ሲል በፌስቡክ ገጹ ጽፏል። የዶክተር ኢሬኒ የቀብር ስነስርዓት ሜሪላንድ በሚገኘው የቀብር ቦታ በዛሬው እለት ይፈጸማል ተብሏል። ዶክተር ኢሬኒ የሁለት ልጆች አባት ነበር።