ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን የት ሊገናኙ ይችላሉ?
በርካታ ዓለማችን ሀገራት በዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት ምክንያት ገለልተኛ አለመሆናቸው ሁለቱ መሪዎች የሚገናኙበት ቦታ ትኩረት ስቧል
ሁለቱ መሪዎች የሚገናኙበት ከተማ ከሰሞኑ ይታወቃል ተብሏል
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ፕሬዝዳንት ፑቲን የት ሊገናኙ ይችላሉ?
ከምርጫ ቅስቀሳቸው ጀምሮ የዩክሬንን ጦርነት እንደሚያስቆሙ ሲናገሩ የቆዩት ፕሬዝዳንት ከሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር በአካል ሊገናኙ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በዩክሬን ጦርነት ምክንያት በርካታ ሀገራት ገለልተኛ አቋም አለመያዛቸው የሁለቱን ሀገራት መገናኛ ቦታ ትኩረት እንዲስብ አድርጎታል፡፡
ሮይተርስ ምንጮቹን በይፋ ባልጠቀሰበት ዘገባው ሪያድ አልያም አቡዳቢ የአሜሪካ እና ሩሲያ ፕሬዝዳንቶች መገናኛ ቦታዎች ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል፡፡
የሩሲያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ከሰሞኑ በሳውዲ አረቢያ የተባበሩት አረብ ኢምሬት ተገኝተው ጉብኝት እንዳደረጉም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ሳውዲ አረቢያ እና የተባሩት አረብ ኢምሬት አሜሪካ እና ሩሲያ በታሪክ ከፍተኛ የጠባለ የእስረኞች ልውውጥ ማድረጋቸው አይዘነጋም፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ዩክሬን እና ሩሲያ የምርኮኞች ልውውጥ በተደጋጋሚ ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን የመሪ ለመሪ ግንኙነቱም ጥሩ በሚባል ደረጃ ላይ እንደሆነም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ሁለቱ የዓለማችን ቀዳሚ ነዳጅ ላኪ ሀገራት ከሩሲያ እና አሜሪካ ጋር ጥሩ የሚባል ግንኙነት ያላቸው ሲሆን በዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ላይ ገለልተኛ አቋምን ይከተላሉ፡፡
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ፕሬዝዳንት ፑቲን ከሰሞኑ የስልክ ውይይት እንደሚያደረጉ የተገለጸ ሲሆን ዝግጅቶች በመጠናቀቅ ላይ እንደሆኑም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡