ብሪትኒ ግሪነር በተጠረጠረችበት ወንጀል ጥፋተኛ ከተባለች እሰከ 10 አመት እስር ይፈረድባታል
አሜሪካዊቷ የቅርጫት ኳስ ኮከብ ብሪትኒ ግሪነር በእፅ ዝውውር ተከሳ በሩሲያ ሞስኮ አቅራቢያ በሚገኝ ፍርድ ቤት ቀረበች።
ብሪትኒ ግሪነር በተጠረጠረችበት ወንጀል ጥፋተኛ ከተባለች እሰከ 10 አመት እስር ይፈረድባታል። ግሪነር በመጀመሪያው የፍርድ ቤት ቀጠሮዋ ሆነ ብሎ ናርኮቲክስን ወደ ሩሲያ በማስገባት መከሰሷ ተነግሯታል።
ተከሳሽ ግሪነር የክሱን ጭብጥ መረዳቷን ብቻ ለፍርድ ቤቱ ተናግራለች፤ ዳኛው በፈረንጆቹ ለሐምሌ ሰባት ቀጠሮ ሰጥቷል።
በሩሲያ እና በአሜሪካው ብሄራዊ የቅርጫት ኳስ ማህበር በመደበኛነት የምትጫወተው የ31 አመቷ ግሪነር በፈረንጆቹ ባለፈው የካቲት ውስጥ ነበር ቦርሳዋ በቫፕ መያዧ ውስጥ ሀሽሽ ይዛለች በሚል የተያዘችው።
ጉዳዩ እየታየ ያለው በዩክሬን ባለው ጦርነት ምክንያት አሜሪካ እና ሩሲያ ከፍተኛ ፍጥጫ በገቡበት ወቅት ነው። አሜሪካ ግሪነር የታሰረችው ያለአግባብ ነው ብላለች።
ግሪነር ከሞሶኮ ወጣ ብሎ በሚገኘው የኪምኪ ከተማ ፍርድ ቤት ነው የቀረበችው።
ግሪነር ፍርድ ቤት በቀረበችበት ወቅት ሶስት የአሜሪካ ኢምባሲ ሰራተኞች ፍርድ ቤት ተገኝተው ተከታትለዋል። ጠበቃዋ በምን መልኩ ሊከራከር እንደሚችል ተጠይቆ መልስ አለመስጠቱን ሮይተርስ ዘግቧል።