አንቶኒ ብሊንከን የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሁኔታ በተመለከተ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ይመክራሉ ተባለ
ስምምነቱ እንዲደረስ አሜሪካ ሚና አንደነበራት ይታወሳል
ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ከአፍሪካ ህብረት አመራሮች ጋር ይመክራሉ ተብሏል
አዲስ አበባ የሚገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ከአፍሪካ ህብረት አመራሮች ጋር ይመክራሉ ተብሏል።
የፌደራል መንግስት እና ህወሓት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በፈረሙት የዘላቂ ግጭት ማቆም ስምምነት ሁኔታ ወጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሊመክሩ ከሚችሉበት ጉዳዮች አንዱ እንደሚሆን ይጠበቃል።
ስምምነቱ እንዲደረስ አሜሪካ ሚና አንደነበራት ይታወሳል።
ሁለት አመት ያስቆጠረውን ጦርነት ማስቆም የቻለውን ስምምነት ያደነቀችው አሜሪካ፣ ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ የተፈጸሙ ወንጀሎችን በተመለከተ ተጠያቂነት መስፈን እንደሚገባ መግለጿ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ መንግስት በሽግግር ፍትህ አማካኝነት በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች መፍትሄ እንደሚያገኙ በመግለጽ ላይ ነው።
መንግስት ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከተመድ ጋር በትብብር የሰራውን የምርመራ ውጤት ከተወሰኑ ነጥቦች ውጭ ያሉትን እንደሚቀበል እና ተጠያቂነት ለማስፈን እንደሚጠቀምበት መግለጹ ይታወሳል።
ነገርግን ኢትዮጵያ የተመድን የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የሰበአዊ መብት ጥሰት መርማሪ ባለሙያዎች የፖለቲካ አላማ ያላቸው ናቸው በማለት በአዎንታ አትመለከታቸውም።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ የባለሙያዎች ቡድኑ የቆይታ ጊዜው እንዳይራፈም እና እንዲበተን ጠይቀል።
አለም አቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች የባለሙያዎቹ የስራ ጊዜ እንዲራዘም እና ኢትዮጵያም እንድትቀበል ጫና እየፈጠሩ ነው።