ፖለቲካ
አሜሪካ የሆውዚ አማጺያን የአሜሪከ ኢምባሲ እና የተመድ ሰራተኞችን እንዲለቁ ጥሪ አቀረበች
ዩኔስኮ እና የተመድ የሰብአዊ መብቶች ድርጅት ሁለት ሰራተኞች እንደተያዙባቸው ገልጸዋል
አሜሪካ ከ12ቱ ውስጥ የኤምባሲ ሰራተኞቹ ምን ያህሉ እንደሆኑ አልገለጸችም
የሆውዚ አማጺያን 12 የሚሆኑ የቀድሞ እና ነባር የአሜሪካና እና የተመድ ሰራተኞችን መያዛቸው ቀጥለዋል ያለችው አሜሪካ አማጺያን እንደ መልከካም እምነት ማሳያ አድርገው ሰራተኞቹን እንዲቀለቋቸው ጥሪ ማቅረቧን ሮተርስ ዘግቧል፡፡
አማጺያኑ ባለፈው ህዳር ወር በየመን ዋና ከተማ ሰንአ ከሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ የመናዊ የሆኑ ሰራተኞችን ማሰራቸውን ማስታወቋ ይታወሳል፡፡
የተመድ ኢዱኬሽናል ሣይንቲፊክ ኤንድ ከልቸራል ኦርጋናይዜሽን(ዩኔስኮ) እና የተመድ የሰብአዊ መብቶች ድርጅት ሁለት ሰራተኞች እንደተያዙባቸው ገልጸዋል፡፡
በየመን የአሜሪካ ተወካይ ቲም ሌንደርኪንግ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት "ሆውዚች በአሁኑ እና የቀድሞ የአሜሪካ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞቻችን 12 ያደረሱትን እስር እናወግዛለን።
"ይህ እስር... እጅግ በጣም አሉታዊ ምልክት ነው። ሆውዚች እነዚህን ግለሰቦች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሲፈቱ የመልካም እምነት ማሳያን ማየት እንፈልጋለን።"
አሜሪካ ከ12ቱ ውስጥ የኤምባሲ ሰራተኞቹ ምን ያህሉ እንደሆኑ አልገለጸችም፡፡