ሩሲያ አውሮፓን በስደተኞች የማጥለቅለቅ እቅድ መንደፏ ተገለጸ
እንደ ዓለም አቀፉ ስደተኞች ማዕከል ከሆነ ሩሲያ በፖላንድና ሉትንያ በኩል ስደተኞችን ወደ አውሮፓ ትልካለች ተብሏል
የሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ስደተኞች ወደ ሩሲያ በካሊኒንግራድ በኩል ወደ ሀገሯ እንዲገቡ ፈቅዳለች ተብሏል
ሩሲያ አውሮፓን በስደተኞች የማጥለቅለቅ እቅድ መንደፏ ተገለጸ።
ዓለም አቀፉ የስደተኞች ፖሊሲ ልማት ኢንስቲትዩት እንዳስታወቀው ሩሲያ አውሮፓን በስደተኞች የማጥለቅለቅ እቅድ እንዳላት ገልጿል።
ዩሮ ኒውስ የኢንስቲትዩቱን መግለጫ ዋቢ እንደዘገበው ከሆነ ሩሲያ በካሊኒንግራድ አውሮፕላን መረፊያ በኩል ስደተኞችን ወደ አውሮፓ እንዲገቡ ልታደርግ ትችላለች ተብሏል።
- አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት የታገዱ የሩሲያ ንብረቶችን ለዩክሬን ሊሰጡ እንደሚችሉ ጠቆሙ
- የምዕራባውያን ታንኮች በዩክሬን ጦርነት የሚያመጡት አንዳች ለውጥ የለም - ሩሲያ
የሩሲያዋ ካሊኒንግራድ ለፖላንድ እና ሉትንያ አዋሳኝ ከተማ ስትሆን የዚች ከተማ አውሮፕላን ጣቢያ ዓለም አቀፍ በረራዎችን ለማድረግ ዝግጁ እንደሆነ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
ሩሲያ የሰሜን አፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ ስደተኞች በካሊልንግራድ ኤርፖርት በኩል ወደ አውሮፓ በመግባት የደህንነት ስጋትን የመፍጠር እቅድ አላት ስለመባሏ እስካሁን ምላሽ አልሰጠችም።
የሩሲያን እቅድ ቀድማ የገመተችው ፖላንድ ከሁለት ሜትር በላይ የሽቦ አጥር በመገንባት ላይ ትገኛለች።
አውሮፓ አሁን ላይ በነዳጅ ዋጋ መናር፣ በኑሮ ውድነት ፣በስራ ማጣት እና በጦርነቱ በተፈናቀሉ ዩክሬናዊያን ምክንያት ጫና ውስጥ ናት የሚለው ኢንስቲትዩቱ በዚህ ሁኔታ ስደተኞችን የማስተናገድ አቅም እንደሌለም አሳስቧል።
በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ምክንያት ስምንት ሚሊዮን ዩክሬናዊያን ወደ አውሮፓ ሀገራት እንደተሰደዱ ተገልጿል።