አሜሪካ እና ቻይና በመካከላቸው ያለውን ውጥረት ለማርገብ ተስማሙ
አሜሪካ እና ቻይና በመካከላቸው ያለው ውጥረት ወደ ግጭት እንዳያመራ ግጭቱን ለማርገብ ተስማምተዋል
የቻይናው ፕሬዝደንት ዢ ጅንፒንግ ብሊንከንን ከተቀበሉ በኋላ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መሻሻል መታየቱን ተናግረዋል
አሜሪካ እና ቻይና በመካከላቸው ያለው ውጥረት ወደ ግጭት እንዳያመራ ግጭቱን ለማርገብ ተስማምተዋል።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ቻይናን ጎብኝተዋል።
ሁለቱ ሀገራት ውጥረቱን ለማርገብ ቢስማሙም፣ ይህ ነው የሚባል ትልቅ ለውጥ አልታየም ተብሏል።
የቻይናው ፕሬዝደንት ዢ ጅንፒንግ ብሊንከንን ከተቀበሉ በኋላ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መሻሻል መታየቱን ተናግረዋል።
በሁለቱ ኃያላን ሀገራት መካከል የሚፈጠረው ግጭት አለምን ሊያናጋ ስለሚችል፣ ሰላማዊ ግንኙነት ማስፈን እንደሚገባ ብሊንከን እና ዢ ገልጸዋል።
የአሜሪካ ማዕቀብ እንቅፋት ነው ያለችው ቻይና ዋሽንግተን የምትፈልገውን ወታደራዊ የግንኙነት መስመር ለመክፈት ፈቃደኛ አልሆነችም።
ሁለቱ ሀገራት በታይዋን ጉዳይ፣ በንግድ እና በዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ከያዙት አቋም ለውጥ አላሳዩም።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት ተሻሽሏል ብለዋል። ይህ መሻሻል የመጣው ብሊንከን ቻይናን በመጎብኘታቸው ነው ብለዋል ፕሬዝደንት ባይደን።
በቻይና የሁለት ቀናት ጉብኝት ያደረጉት ብሊንከን ስጋቶችን በቀጥታ በማንሳት፣ ለንግግር መንገድ በማመቻቸት እና የትብብር ጉዳዮችን በመለየት ስኬታማ ነበር ብለዋል።
ብሊንከን ከፈረንጆቹ 2018 ወዲህ ቻይናን የጎበኙ የመጀመሪያው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ናቸው።