የድቪ 2026 ማመልከቻ መቼ ይጀመራል?
የድቪ 2025 እድለኞች ከያዝነው መስከረም ወር በኋላ የቪዛ ጥያቄ ማቅረብ ይጀምራሉ
አሜሪካ ከ1995 ጀምሮ በየዓመቱ 55 ሺህ ሰዎችን ወደ ሀገሯ በመውሰድ ላይ ናት
የድቪ 2026 ማመልከቻ መቼ ይጀመራል?
የዓለማችን ልዕለ ሀያል የሆነችው አሜሪካ ከፈረንጆቹ 1995 ዓመት ጀምሮ በድቪ ሎተሪ አማካኝነት ወደ ሀገሯ በመውሰድ ለይ ትገኛለች፡፡
ኢትዮጵያ ለዚህ እድል ከተፈቀደላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን በየዓመቱ በአማካኝ ከ4 ሺህ እስከ 5 ሺህ ኢትዮጵያዊያን ወደ አሜሪካ ያቀናሉ፡፡
የድቪ 2024 እድለኛ ኢትዮጵያዊን የቪዛ ማመልከቻቸው ከጥቂት ቀናት በኋላ የሚያበቃ ሲሆን የድቪ 2025 እድለኞች ደግሞ ከያዝነው መስከረም ወር መጠናቀቅ በኋላ ወደ አሜሪካ ለመጓዝ የቪዛ ጥያቄያቸውን ማቅረብ ይጀምራሉ፡፡
ይህ በዚህ እንዳለም የድቪ 2026 የማመልከቻ ጊዜ ከአንድ ሳምንት በኋላ የሚጀመር ሲሆን ለአንድ ወር እንደሚቆይ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት አስታውቋል፡፡
የማመልከቻ ጊዜው ከመስከረም 21 ቀን እስከ ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት 30 ቀናት ይቆያል የተባለ ሲሆን አሸናፊ እድለኞች ደግሞ ግንቦት ወር ጀምሮ ማወቅ እንደሚቻልም ተገልጿል፡፡
የድቪ 2025 አመልካቾች አሸናፊ እድለኞች ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ ይፋ የተደረገ ሲሆን አፍሪካ፣ እስያ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አውስትራሊያ የዚህ እድል ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡
አፍሪካ የዚህ እድል ትልቁን ኮታ የምትሸፍን ሲሆን በዲቪ 2022 ፕሮግራም ግብጽ፣ አልጀሪያ እና ሱዳን እያንዳንዳቸው 6 ሺህ ሰዎች እድለኞች ሲሆኑ ሞሮኮ 4 ሺህ 138 ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ 3 ሺህ 347 ፣ጋና 3 ሺህ 145 ፣ ኢትዮጵያ ደግሞ 2 ሺህ 988 ሰዎች የዲቪ እድለኛ እንደሆኑ ከተቋሙ ድረገጽ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።