አሜሪካ ዩክሬን የተሰጠችውን ክለስተር ቦንብ ጥቅም ላይ እያዋለች መሆኑን ማረጋጠጧን ገለጸች
ሩሲያ በቂ የሆነ የክለስተር ቦንብ እንዳላት እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ልትጠቀምበት እንደምትችል መግለጿ ይታወሳል
ፕሬዝደንት ባይደን አሜሪካ ለዩክሬን ክለስተር ቦንብ ለመስጠት ያሳለፈችው ውሳኔ "ከባድ ውሳኔ" ነው ማለታቸው ይታወሳል
ኋይት ሀውስ ዩክሬን አሜሪካ የሰጠቻትን የክለስተር ቦንብ በሩሲያ ጦር ላይ ውጣታማ በሆኑ መልኩ እየተጠቀመችበት መሆኑን አረጋግጫለሁ ማለቱን ቢቢሲ ዘግቧል።
የአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጆን ክርቢይ ዩክሬን በሩሲያ ይዞታዎች ላይ በምታደርገው ጥቃት እና ዘመቻ በደንብ እየተጠቀመችበት ነው ብለዋል።
የክለስተር ቦንድ ሲፈነዳ በርካታ ቦንቦች ወደ ብዙ ቦታ ስለሚፈነጣጠሩ በንጹሃን ላይ ጉዳት ያደርሳል በሚል በ100 ሀገራት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ታግዶ ነበር።
አሜሪካ ዩክሬንን የማጥቃት አቅም ለመጨመር ነበር የክለስተር ቦንብ የለገሰቻት።
ዩክሬን ይህን ቦንብ የምጠቀመው የሩሲያ ጦር የተከማቸበትን ቦታ ለማስለቀቅ ብቻ ነው ስትል ቃል መግባቷ ይታወሳል።
ክርቢይ እንደገለጹት ዩክሬን ቦንቡን በአግባቡ እየተጠቀመችበት ነው።
"ቦንቡን በአግባቡ እየተጠቀሙበት ነው፤ በርግጥም በሩሲያ ጦር አሰላለፍ እና እንቅስቃሴ ላይ ለውጥ አምጥቷል።"ብለዋል ቃል አቀባዩ።
አሜሪካ ለዩክሬን የክለስተር ቦንብ ለመላክ የወሰነችው፣ዩክሬን በጀመረችው የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ የተተኳሽ ክምችት እያለቀባት መሆኑን መግለጿን ተከትሎ ነው።
አሜሪካ ለዩክሬን ክለስተር ቦንብ ለመስጠት ያሳለፈችው ውሳኔ "ከባድ ውሳኔ" ነው ማለታቸው ይታወሳል።
የአሜሪካ አጋሮች ካናዳ፣ ዩክ እና ኒውዝላንድ ለዩክሬን የክለስተር ቦንብ ማስታጠቅን አይደግፉም።
ሩሲያ በቂ የሆነ የክለስተር ቦንብ እንዳላት እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ልትጠቀምበት እንደምትችል መግለጿ ይታወሳል።