በአሜሪካ ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ለመሆን እስከ 1 ሚሊየን ዶላር ጉቦ መስጠት “የግድ ነው” ተባለ
የፖሊሲ ክርክሮች “በሙስና ተጨማልቀዋል” ተብሏል
የአላባማው ተወካይ ልዩ ፍላጎት ያላቸው አካላት አሜሪካን እየዘወሩ እንደሆነ ገለጹ
በአሜሪካ ምክር ቤት ውስጥ ዋነኛ ቋሚ ኮሚቴ የሚባሉትን በሊቀመንበርነት ለመምራት ጉቦ መስጠት የተለመደ ሆኗል ተባለ።
በምክር ቤት ውስጥ ሁነኛና ጠቃሚ ናቸው የተባሉ ኮሚቴዎችን በሰብሳቢነት ለመምራት ጉቦ መስጠት እንደሚስፈልግ መታዘባቸውን የአላባማ ተወካይ ተናረዋል።
ሞ ብሩክ የተባሉት የአላባማ ተወካይ ደጋፊዎቻቸውን ሰብስበው እንደተናገሩት የኮሚቴዎች መቀመጫ በገንዘብ የሚገዙ እንደሆኑ ገልጸውላቸዋል።
የኮንግረንስ መወመጫዎች በተለይም ጠቃሚ የሚባሉት ልዩ ፍላጎት ባላቸው ቡድኖች የሚዘወር እንደሆነም ነው ተወካዩ ያነሱት።
ተወካዩ፤ የኮሚቴዎቹ አባልና ሰብሳቢ ለመሆን እስከ 1 ሚሊየን ዶላር ገንዘብ እንደሚከፈልም ለደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል ተብሏል።
የኮሚቴ ሰብሳቢ ለመሆን ጉቦ መስጠት የብዙ አሜሪካውያን ፍላጎት በምክር ቤቱ እንዳያልፍ እንደሚያደርግም ነው የአላባማው ተወካይ የተናገሩት።
ተወካዩ ይህንን የሙስና ጉዳይ መሸፋፈን እንደማይገባና በግልጽ መናገር ግደታ እንደሆነ ጠቅሰዋል። ይህንን ጉቦ የመስጠት ስራ የሚያከናውኑት ደግሞ ከተጽዕኖ ፈጣሪዎች እርዳታ የሚቀበሉ ቡድኖች ናቸውም ብለዋል።
ልዩ ፍላጎት ያላቸው አካላት አሜሪካን እየዘወሩ እንደሆነ የሚናገሩት ተወካዩ ይህንን ደግሞ በግልጽ መናገር ግደታቸው እንደሆነ አንስተዋል። ተወካዩ ይህንን ያሉበት ተንቀሳቃሽ ምስል ትናንትና ጀምሮ በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተሰራጨ ነው።
ሕግ አውጭ አባላት አንድን ቋሚ ኮሚቴ መምራት ከፈለጉ የግድ ጎቦ መስጠት እንዳለባቸውም ነው የተጠቀሰው። ይህ ደግሞ ለብሔራዊ የሪፐብሊካን ኮንግረንስ ኮሚቴ እና ለዴሞክራቶች ኮንግረንስ ኮሚቴ እንደሚሰራም ነው የተገለጸው።
የቋሚ ኮሚቴ መሪ ለመሆን የሚሰጠው ጉቦ እንደ ቋሚ ኮሚቴዎቹ ወሳኝነትና ጠቃሚነት እንደሚወሰንም ነው ተወካዩ የገለጹት። ይህ የጎቦ አሰራር የሚያመለክተው የፖሊሲ ክርክሮች በሙስና እንደተጨማለዉ ነው ሲሉም ነው የተናገሩት።